የለወጠኝን (Yelewetegnen) - ሶፍያ ፡ ሽባባው

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሶፍያ ፡ ሽባባው
(Sofia Shibabaw)

Sofia Shibabaw 1.jpg


(1)

ፍቅር ፡ ከመቃብር ፡ በላይ
(Feqer Kemeqaber Belay)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፮ (2003)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 4:48
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሶፍያ ፡ ሽባባው ፡ አልበሞች
(Albums by Sofia Shibabaw)

እስኪ ፡ አክብሩልኝ ፡ የለወጠኝን (፪x)
አዲስ ፡ ስም ፡ ሰጥቶ ፡ የቀየረኝን (፪x)
ከማይጠፋው ፡ ዘር ፡ የወለደኝን (፪x)
ለቤቱ ፡ አገልጋይ ፡ ያደረገኝን (፪x)

እኔም ፡ ላክብረው ፡ ባለው ፡ ዘመኔ
ላዳነኝ ፡ ለርሱ ፡ ለዚህ ፡ መድህኔ
ብዘምርለት ፡ ሁሌ ፡ ብናገር
አይበዛበትም ፡ ላረገው ፡ ነገር

ስንቱን ፡ አውርቼ ፡ የቱን ፡ ልተው ፡ ውለታው ፡ በዝቷል (፪x)
የማዳኑን ፡ ክንድ ፡ በእኔ ፡ ለፍጥረት ፡ ገልጧል (፪x)
የእኔን ፡ መለወጥ ፡ ያየ ፡ ይበል ፡ አይበቃም (፪x)
ገና ፡ እጁ ፡ አላጠረም ፡ ያድናል ፡ ሌላም (፪x)

ክሩ ፡ በመርፌ ፡ የገባለት ፡ ሰው (፪x)
የዓይኑም ፡ እምባ ፡ ፈሶ ፡ የታበሰው (፪x)
በሩጫ ፡ ሜዳ ፡ መስመር ፡ ከያዘ (፪x)
ደካማው ፡ ሲወድቅ ፡ ብርቱው ፡ ካገዘ (፪x)

በመከናወን ፡ ማን ፡ ቅር ፡ ይሰኛል
አእምሮ ፡ ከሌለው ፡ ግን ፡ ቅር ፡ ይለዋል
ማሰብ ፡ የሚችል ፡ አእምሮው ፡ ጤነኛ
መከናወንን ፡ ይወዳልና

ታዲያ ፡ ምነው ፡ ቅር ፡ አላችሁ ፡ ስይዝ ፡ መስመሩን (፪x)
መከናወን ፡ ሲሆንልኝ ፡ ሲያወርሰኝ ፡ ክብሩን (፪x)
ከዚያ ፡ ካስጨናቂው ፡ አለም ፡ ሳመልጥ ፡ በርሬ (፪x)
ተከትሎኝ ፡ መምጣት ፡ እንጂ ፡ አይጠቅምም ፡ ወሬ (፪x)

ዕድሜዬን ፡ ሲጨምር ፡ ዓመት ፡ ሲበዛ (፪x)
ሲያሸጋግረኝ ፡ መስሎኝ ፡ የዋዛ (፪x)
ስቀልድባት ፡ በሕይወቴ ፡ ላይ (፪x)
መቼ ፡ አስቻለው ፡ ሲያየኝ ፡ ከሰማይ (፪x)

ለካ ፡ አስቀድሞ ፡ አስቦኝ ፡ ኖሯል
የመለወጤ ፡ ጊዜያቱ ፡ ደርሷል
እርሱ ፡ የመደበው ፡ ሰዓቱ ፡ አያልፍ
ጌታ ፡ ኢየሱሴን ፡ አግኝቼው ፡ ሳላርፍ

እኔም ፡ አላለፍኩ ፡ ከቀኑ ፡ ተማረኩለት (፪x)
የርሱ ፡ ፍቅር ፡ አይሎ ፡ እንጂ ፡ ምን ፡ አረግኩለት (፪x)
ምን ፡ አይቶብኝ ፡ ነው ፡ እንዳልል ፡ ራሱን ፡ አይቶ ፡ ነው (፪x)
ለውጦ ፡ ከቀያየረኝ ፡ ከልካዩስ ፡ ማነው (፪x)