From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ ኦ ፡ እኔ ፡ ማነኝ
ቤቴስ : ምንድነው (፪x)
የሰማዩን ፡ ዜማ ፡ ዝማሬ
የፅድቅን ፡ ቅኔ ፡ አውቄ ፡ ተምሬ
እንድኖር ፡ ልብህ ፡ የፈቀደው
አምላክ ፡ ሆይ ፡ እኔ ፡ ማነኝ
ቤቴስ ፡ ምንድነው (፪x)
አውቃለሁ ፡ የእኔ ፡ ማንነቴን
የትውልድ ፡ ሐረግና ፡ ቤቴን
ለዚህ ፡ ልታበቃኝ ፡ የቻልከው
ካንተ ፡ የተነሳ ፡ ብቻ ፡ ነው
ይገርመኛል ፡ እስካሁን ፡ ድረስ
በቤትህ ፡ ቆሜ ፡ ስመላለስ
የተከልከኝ ፡ በቅዱስ ፡ ቃልህ
ስራህ ፡ ይደንቀኛል ፡ ምህረትህ
አዝ፦ ኦ ፡ እኔ ፡ ማነኝ
ቤቴስ ፡ ምንድነው
የሰማዩን ፡ ዜማ ፡ ዝማሬ
የፅድቅን ፡ ቅኔ ፡ አውቄ ፡ ተምሬ
እንድኖር ፡ ልብህ ፡ የፈቀደው
ጌታ ፡ ሆይ ፡ እኔ ፡ ማነኝ
ቤቴስ ፡ ምንድነው (፪x)
ቅኔ ፡ ውሃ ፡ አይደል ፡ በነፃ
የሚቀዳ ፡ አይደለም ፡ ከጓዳ
የሚፈልቅ ፡ እንጂ ፡ ከሆዴ ፡ ውስጥ
የማይደርቅ ፡ አረከው ፡ እንደ ፡ ምንጭ
ሰው ፡ ፊት ፡ ዘመርኩ ፡ እንጂ ፡ ላንተ ፡ ነው
ምስጋና ፡ አምልኮ ፡ የማቀርበው
የምትቀበለኝ ፡ አንተ ፡ ነህ
ምርጫህ ፡ ተስማምቶኛል ፡ የእኔ ነህ
አዝ፦ ኦ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ አመልክሃለሁ
ከመረጥከኝ ፡ ዘምሪ ፡ ብለህ
ልትሰማው ፡ ድምፄን ፡ ከፈለክ
ምስጋና ፡ አምልኮዬን ፡ ከወደድክ
በእውነት ፡ እና: በመንፈስ ፡ ሆኜ
ላምልክህ ፡ ላክብርህ ፡ ቆሜ ፡ ውዱ ፡ ጌታዬ (፪x)
መለወጤን ፡ ሲያዩ ፡ በዓይናቸው
የቀደሞው ፡ እየታወሳቸው
ሁለት ፡ የሆንኩኝ ፡ መሰላቸው
የውስጤንስ ፡ ማን ፡ ባሳያቸው
የተከልከኝን ፡ እኔ ፡ አውቃለሁ
በፍቅርህ ፡ ገመድ ፡ ታስሬአለሁ
አልቆልኛል ፡ ከእንግዲህ ፡ በቃ
የፊት ፡ ነው ፡ እርምጃዬ ፡ ከአንተ ፡ ጋ
አዝ፦ ኦ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ አመልክሃለሁ
ከመረጥከኝ ፡ ዘምሪ ፡ ብለህ
ልትሰማው ፡ ድምፄን ፡ ከፈለግክ
ምስጋና ፡ አምልኮዬን ፡ ከወደድክ
በእውነትና ፡ መንፈስ ፡ ላምልክህ ፡ ቆሜ (፪x)
|