From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ ፡ እውነተኛ ፡ ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ (፪x)
የማይቀበል ፡ ጉቦ ፡ መማጸኛ
ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ ፡ እውነተኛ ፡ ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ
በቅን ፡ የሚፈርድ ፡ የማይወናበድ
ግራና ፡ ቀኙን ፡ አይቶ ፡ ማይዘላብድ
ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ ፡ እውነተኛ ፡ ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ (፪x)
ነፃ ፡ አወጣኝ ፡ ሆኖ ፡ ጠበቃ
ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ ፡ እውነተኛ ፡ ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ
ከሳሼ ፡ ተነስቶ ፡ ሴራውን ፡ መስርቶ
የጠቀመኝ ፡ መስሎ ፡ ጐትጉቶ ፡ ጐትጉቶ
ሴራውም ፡ ተሳክቶ ፡ እኔንም ፡ አስቶ
መልሶ ፡ ከሰሰኝ ፡ እንዲፈረድብኝ
ከዳኛው ፡ አቆመኝ ፡ ጠበቃ ፡ ሳይኖረኝ
የችሎቱም ፡ ዳኛ ፡ አባቴ ፡ ሆነና
ተከስሼ ፡ ስቀርብ ፡ በልቡ ፡ አዘነና
ሞታ ፡ አትቀርም ፡ እሷ ፡ ብሎ ፡ አሰበና
ሞቷን ፡ እሞታለሁ ፡ ብሎ ፡ በየነልኝ
በኔው ፡ ሐጥያት ፡ እርሱ ፡ ጌታዬ ፡ ሞተልኝ
ሞተልኝ ፡ ሞተልኝ ፡ ሞተልኝ ፡ ጌታዬ ፡ ታደገኝ
ሞተልኝ ፡ ሞተልኝ ፡ ሞተልኝ ፡ ኢየሱሴ ፡ ታደገኝ
አዝ፦ ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ ፡ እውነተኛ ፡ ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ (፪x)
የማይቀበል ፡ ጉቦ ፡ መማጸኛ
ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ ፡ እውነተኛ ፡ ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ
በቅን ፡ የሚፈርድ ፡ የማይወናበድ
ግራና ፡ ቀኙን ፡ አይቶ ፡ የማይዘላብድ
አዝ፦ ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ ፡ እውነተኛ ፡ ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ (፪x)
ነፃ ፡ አወጣኝ ፡ ሆኖ ፡ ጠበቃ
ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ ፡ እውነተኛ ፡ ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ
ነፍሴን ፡ እንደ ፡ ጭልፊት ፡ ሲነዳት ፡ ከፊት ፡ ፊት
ወስዶ ፡ ቢከሳትም ፡ ትልቁ ፡ ዳኛ ፡ ፊት
ከነአደፈው ፡ ልብሴ ፡ ተጐናጽፋ ፡ ነፍሴ
ገልጦ ፡ ገበናዬን ፡ አሳይቶ ፡ ጉዴን
ሊያሳጣኝ ፡ ከችሎት ፡ ያዋረደኝ ፡ መስሎት
እድፋሙ ፡ ጥምጣም ፡ ቢታሰርም ፡ በጣም
አዘዘ ፡ ግን ፡ ዳኛው ፡ ፍርድ ፡ እስከ ፡ ወዲያኛው
ይፈታ ፡ ጥምጣሙ ፡ ኮተታ ፡ ኮተቱ
እንኪ ፡ አዲሱ ፡ ልብስሽ ፡ ታዪ ፡ ተጐናጽፈሽ
ወጥተሻል ፡ አርነት ፡ ሂጂ ፡ በነፃነት
አርነት ፡ አርነት ፡ አርነት ፡ ሄድኩኝ ፡ በነፃነት
አርነት ፡ አርነት ፡ አርነት ፡ ወጣሁ ፡ በነፃነት
አዝ፦ ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ ፡ እውነተኛ ፡ ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ (፪x)
የማይቀበል ፡ ጉቦ ፡ መማጸኛ
ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ ፡ እውነተኛ ፡ ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ
በቅን ፡ የሚፈርድ ፡ የማይወናበድ
ግራና ፡ ቀኙን ፡ አይቶ ፡ የማይዘላብድ
ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ ፡ እውነተኛ ፡ ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ (፪x)
ነፃ ፡ አወጣኝ ፡ ሆኖ ፡ ጠበቃ
ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ ፡ እውነተኛ ፡ ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ
ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ ፡ እውነተኛ ፡ ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ (፬x)
|