ለሕይወትህ ፡ ዋጋ ፡ ስጥ (Lehiwoteh Waga Set) - ሶፍያ ፡ ሽባባው

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሶፍያ ፡ ሽባባው
(Sofia Shibabaw)

Sofia Shibabaw 1.jpg


(1)

ፍቅር ፡ ከመቃብር ፡ በላይ
(Feqer Kemeqaber Belay)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፮ (2003)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 5:59
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሶፍያ ፡ ሽባባው ፡ አልበሞች
(Albums by Sofia Shibabaw)

የባህሪ ፡ ለውጥ ፡ አምጣ (፬x)
ከየት ፡ ይምጣ ፡ ከየት ፡ ይምጣ
ሰው ፡ ሁሉ ፡ ካለበት ፡ ሱስ ፡ ካልወጣ
ከየት ፡ ይምጣ ፡ ከየት ፡ ይምጣ
ሰው ፡ ሁሉ ፡ ደፍሮ ፡ እውነቱን ፡ ካላወጣ (፪x)

ለሕይወትህ ፡ ዋጋ ፡ ስጥ (፫x)
የእድሜ ፡ ማራዘሚያው ፡ ነው ፡ ዋጋው ፡ ውድ
አስቀድመህ ፡ በመጠንቀቅ ፡ በመወሰን ፡ በመለወጥ
ዋጋህን ፡ ውድ ፡ አርገው ፡ የአንተን ፡ ማንነት (፪x)

እንዴት ፡ ሰው ፡ እያወቀ (፪x)
እያወቀ ፡ ሁሉም ፡ አለቀ
እንዴት ፡ ሰው ፡ እየሰማ (፪x)
እየሰማ ፡ ምነው ፡ አልተስማማ

(ቢሰማ ፡ ግን) ፡ ይታቀብ ፡ ነበር
(ቢሰማ ፡ ግን) ፡ ይታመን ፡ ነበር
(ቢሰማ ፡ ግን) ፡ ይጠነቀቅ ፡ ነበር
(ቢሰማ ፡ ግን) ፡ ያመልጠው ፡ ነበር
ባጠገቡ ፡ ያለውን ፡ ሲያጣ
ከደጃፉ ፡ ሁሉም ፡ ሲቀጣ
ይህን ፡ አይቶ ፡ ምነው ፡ ቢመለስ
ተራው ፡ ዞሮ ፡ ለርሱ ፡ ሳይደርስ

እንዴት ፡ ሰው ፡ እያወቀ (፪x)
እያወቀ ፡ ሁሉም ፡ አለቀ
እንዴት ፡ ሰው ፡ እየሰማ (፪x)
እየሰማ ፡ ምነው ፡ አልተስማማ

(ቢሰማ ፡ ግን) ፡ ይታቀብ ፡ ነበር
(ቢሰማ ፡ ግን) ፡ ይታመን ፡ ነበር
(ቢሰማ ፡ ግን) ፡ ይጠነቀቅ ፡ ነበር
(ቢሰማ ፡ ግን) ፡ ያመልጠው ፡ ነበር
ባጠገቡ ፡ ያለውን ፡ ሲያጣ
ከደጃፉ ፡ ሁሉም ፡ ሲቀጣ
ይህን ፡ አይቶ ፡ ምነው ፡ ቢመለስ
ተራው ፡ ዞሮ ፡ ለርሱ ፡ ሳይደርስ

እንዴት ፡ ሰው ፡ እያወቀ (፪x)
እያወቀ ፡ ሁሉም ፡ አለቀ
እንዴት ፡ ሰው ፡ እየሰማ (፪x)
እየሰማ ፡ ምነው ፡ አልተስማማ

የባህሪ ፡ ለውጥ ፡ አምጣ (፬x)
ከየት ፡ ይምጣ ፡ ከየት ፡ ይምጣ
ሰው ፡ ሁሉ ፡ ካለበት ፡ ሱስ ፡ ካልወጣ
ከየት ፡ ይምጣ ፡ ከየት ፡ ይምጣ
ሰው ፡ ሁሉ ፡ ደፍሮ ፡ እውነቱን ፡ ካላወጣ (፪x)

ባህሪህም ፡ ያለው ፡ ስሜት ፡ ህም ፡ ያለው
ፈቃድህም ፡ ያለው ፡ በአንተ ፡ ውስጥ ፡ ነው
(ነው ፡ ነው ፡ ነው ፡ በአንተ ፡ ውስጥ ፡ ነው)
ባለቤቱ ፡ አንተ ፡ እንጂ ፡ ባህሪህ ፡ አይደለም
አለቃው ፡ እንተ ፡ ነህ ፡ ሌላ ፡ ማንም ፡ የለም
(የለም ፡ የለም ፡ ሌላ ፡ ማንም ፡ የለም)

አንተ ፡ ስትጸዳ ፡ አካባቢህ ፡ ይጸዳል
አንተ ፡ ስትለወጥ ፡ ባህሪህ ፡ ይለወጣል
(ይቀያየራል ፡ ሁሉም ፡ ይታደሳል)
(አዲስ ፡ ይሆናል ፡ ሕይወት ፡ ይጣፍጣል)

ተስፋ ፡ የቆረጠ ፡ ሊሞት ፡ ለመሰለ
ለሰው ፡ የሚራራ ፡ የሚለውጥ ፡ አለ
(አለ ፡ አለ ፡ ሰሚ ፡ ካለ ፡ የሚለወጥ ፡ ካለ
አለ ፡ አለ ፡ የሚለውጥ ፡ አለ) ፪x