ክበርልኝ (Keberelegn) - ሶፍያ ፡ ሽባባው

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሶፍያ ፡ ሽባባው
(Sofia Shibabaw)

Sofia Shibabaw 1.jpg

(1)

ፍቅር ፡ ከመቃብር ፡ በላይ
(Feqer Kemeqaber Belay)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፮ (2003)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 6:08
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሶፍያ ፡ ሽባባው ፡ አልበሞች
(Albums by Sofia Shibabaw)

በጨለማ ፡ እያለሁ ፡ ነፍሴ ፡ ተንከራትታ ፡ መቼ ፡ ተውከኝ ፡ የኔ ፡ ጌታ (፪x)
የሰይጣን ፡ ምርኮኛ ፡ ሆኜ ፡ የተጠቃሁ ፡ አወጣኸኝ ፡ የኔ ፡ ጌታ (፪x)
ብቻዬን ፡ ሳለቅስ ፡ ሁሌ ፡ ጠዋት ፡ ማታ ፡ ስጮህ ፡ ብዬ ፡ የኔ ፡ ጌታ (፪x)
ድምጼን ፡ ሰምተህ ፡ ደረስክ ፡ ሳትቆይ ፡ እስከማታ ፡ ክበርልኝ ፡ የኔ ፡ ጌታ (፪x)

አዝ፦ እኔ ፡ ያልዘመርኩኝ ፡ ማን ፡ ይዘምርልህ ፡ ላረግክልኝ ፡ ነገር
ከቶ ፡ እንዲህ ፡ በቀላል ፡ ተዘርዝሮ ፡ አያልቅም ፡ ምህረትህ ፡ ቢቆጠር
ትንሽ ፡ ከቀለለኝ ፡ ብዬ ፡ እንጂ ፡ አያልቅም ፡ ብዘምር ፡ ባወራ
ስላረግከው ፡ ተዓምር ፡ ስላሸጋገርከኝ ፡ ያንን ፡ ተራራ

በጠላቴ ፡ መንግስት ፡ በእቅዱ ፡ ውስጥ ፡ ሆኜ ፡ አይተኸኛል ፡ መድኃኒቴ (፪x)
አወጣኸኝ ፡ ከእጁ ፡ ሳትጠፋ ፡ ሕይወቴ ፡ ክበርልኝ ፡ መድኃኒቴ (፪x)
ልትጠቀምብኝ ፡ በኔ ፡ ልትሰራ ፡ ፈልገህ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ ጌታ (፪x)
ነጥቀህ ፡ የታደግከኝ ፡ ከዚያ ፡ ባለ ፡ ጋራ ፡ ክበርልኝ ፡ የኔ ፡ ጌታ (፪x)

አዝ፦ እኔ ፡ ያልዘመርኩኝ ፡ ማን ፡ ይዘምርልህ ፡ ላረግክልኝ ፡ ነገር
ከቶ ፡ እንዲህ ፡ በቀላል ፡ ተዘርዝሮ ፡ አያልቅም ፡ ምህረትህ ፡ ቢቆጠር
ትንሽ ፡ ከቀለለኝ ፡ ብዬ ፡ እንጂ ፡ አያልቅም ፡ ብዘምር ፡ ባወራ
ስላረግከው ፡ ተዓምር ፡ ስላሸጋገርከኝ ፡ ያንን ፡ ተራራ

ለኃጥዕ ፡ ለጻድቅ ፡ ፀሐይህ ፡ ይወጣል ፡ ለፍጥረትህ ፡ ሁሉ ፡ ይወጣል (፪x)
ቸርነትህ ፡ ፍቅርህ ፡ መች ፡ ይበላለጣል ፡ ለሁሉም ፡ ሰው ፡ ሰጥተኸዋል (፪x)
ለኔ ፡ ግን ፡ አወጣህ ፡ ብርሃን ፡ ሌላ ፡ ፀሐይ ፡ ካልጠበቅኩት ፡ አቅጣጫ ፡ ላይ (፪x)
የንጋቱ ፡ ኮከብ ፡ ወልድ ፡ ወረደ ፡ ከላይ ፡ ክበርልኝ ፡ በምድር ፡ በሰማይ (፪x)

አዝ፦ እኔ ፡ ያልዘመርኩኝ ፡ ማን ፡ ይዘምርልህ ፡ ላረግክልኝ ፡ ነገር
ከቶ ፡ እንዲህ ፡ በቀላል ፡ ተዘርዝሮ ፡ አያልቅም ፡ ምህረትህ ፡ ቢቆጠር
ትንሽ ፡ ከቀለለኝ ፡ ብዬ ፡ እንጂ ፡ አያልቅም ፡ ብዘምር ፡ ባወራ
ስላረግከው ፡ ተዓምር ፡ ስላሸጋገርከኝ ፡ ያንን ፡ ተራራ