ፍቅሬ ፡ እጅግ ፡ ጨመረ (Feqrie Ejeg Chemere) - ሶፍያ ፡ ሽባባው

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሶፍያ ፡ ሽባባው
(Sofia Shibabaw)

Sofia Shibabaw 1.jpg


(1)

ፍቅር ፡ ከመቃብር ፡ በላይ
(Feqer Kemeqaber Belay)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፮ (2003)
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 7:10
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሶፍያ ፡ ሽባባው ፡ አልበሞች
(Albums by Sofia Shibabaw)

ውዴ ፡ እንዳንተ ፡ ወዳጅ ፡ ከቶ ፡ የት ፡ ይገኛል

አዝ፦ ፍቅሬ ፡ እጅግ ፡ ጨመረ ፡ ናፍቆቴም ፡ በረታ (፪x)
ናልኝ ፡ የኔ ፡ ፍቅር ፡ ናልኝ ፡ የእኔ ፡ ጌታ (፪x)
ኢየሱሴ ፡ ስልህ ፡ ላፌ ፡ ይጣፍጠኛል
ውዴ ፡ እንዳንተ ፡ ወዳጅ ፡ ከቶ ፡ የት ፡ ይገኛል
ለእኔ ፡ የት ፡ ይገኛል

ቃልህ ፡ እጅግ ፡ ጣፋጭ ፡ እንደ ፡ ማር ፡ ወለላ
ሰላም ፡ ይሰጠኛል ፡ በልቤ ፡ እየሞላ
ሰይፍህ ፡ ነውሬን ፡ ከላይ ፡ አስወግዶ
በቃልህ ፡ አስዋብከኝ ፡ ልብህ ፡ ልቤን ፡ ወዶ (፪x)

አዝ፦ ፍቅሬ ፡ እጅግ ፡ ጨመረ ፡ ናፍቆቴም ፡ በረታ (፪x)
ናልኝ ፡ የኔ ፡ ፍቅር ፡ ናልኝ ፡ የእኔ ፡ ጌታ (፪x)
ኢየሱሴ ፡ ስልህ ፡ ላፌ ፡ ይጣፍጠኛል
ውዴ ፡ እንዳንተ ፡ ወዳጅ ፡ ከቶ ፡ የት ፡ ይገኛል
ለእኔ ፡ የት ፡ ይገኛል

ውዴ ፡ እንዳንተ ፡ ወዳጅ ፡ እንዳንተ ፡ ወዳጅ

አስተዋይ ፡ አረገኝ ፡ አስተዋዩ ፡ አባቴ
የፈገግታዬ ፡ ምንጭ ፡ የደስታ ፡ ምክንያቴ
ኢየሱስ ፡ መድህኔ ፡ ውበት ፡ ደም ፡ ግባቴ
ጌታዬ ፡ ደምህ ፡ ነው ፡ የልጅነት ፡ መብቴ (፪x)

አዝ፦ ፍቅሬ ፡ እጅግ ፡ ጨመረ ፡ ናፍቆቴም ፡ በረታ (፪x)
ናልኝ ፡ የኔ ፡ ፍቅር ፡ ናልኝ ፡ የእኔ ፡ ጌታ (፪x)
ኢየሱሴ ፡ ስልህ ፡ ላፌ ፡ ይጣፍጠኛል
ውዴ ፡ እንዳንተ ፡ ወዳጅ ፡ ከቶ ፡ የት ፡ ይገኛል
ለእኔ ፡ የት ፡ ይገኛል

ውዴ ፡ እንዳንተ ፡ ወዳጅ ፡ እንዳንተ ፡ ወዳጅ