ፍቅር ፡ ከመቃብር ፡ በላይ (Feqer Kemeqaber Belay) - ሶፍያ ፡ ሽባባው

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሶፍያ ፡ ሽባባው
(Sofia Shibabaw)

Sofia Shibabaw 1.jpg


(1)

ፍቅር ፡ ከመቃብር ፡ በላይ
(Feqer Kemeqaber Belay)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፮ (2003)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 5:04
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሶፍያ ፡ ሽባባው ፡ አልበሞች
(Albums by Sofia Shibabaw)

አዝፍቅር ፡ እስከ ፡ መቃብር (፬x)
የስንቶች ፡ ፍቅር ፡ እስከ ፡ መቃብር
የኛ ፡ ግን ፡ ኢየሱስ ፡ የኛ ፡ ግን ፡ ኤልሻዳይ
የርሱ ፡ ፍቅር ፡ ያልፋል ፡ ከመቃብር ፡ በላይ
ፍቅር ፡ ያልፋል ፡ ከመቃብር (፬x)

ፍቅርን ፡ የተራበ ፡ ፍቅርን ፡ የተጠማ ፡ ከውስጡ ፡ ካንጀቱ
ስለፍቅር ፡ አይነት ፡ ቢሰማ ፡ አይሰለቸው ፡ ተርቧል ፡ ከእውነቱ
አውቋል ፡ አንድ ፡ ነገር ፡ የፍቅርን ፡ መቋጫ ፡ የመጨረሻውን
ከመቃብር ፡ ድረስ ፡ የገባውን ፡ ኪዳን ፡ ውሉን ፡ ማስረጃውን

ግን ፡ ደግሞ ፡ አለ ፡ ሌላ ፡ መቃብር ፡ ያለፈ ፡ ፍቅሩ ፡ ያልተሸነፈ
በፍቅር ፡ ተይዞ ፡ ያለምክንያት ፡ ወርዶ ፡ ከመቃብር ፡ ማዶ
ተቀብሮ ፡ ያልቀረ ፡ ጥሶ ፡ የተሻገረ ፡ ጭራሹን ፡ ያረገ
ሞቶ ፡ የተነሳ ፡ ሃዘን ፡ የሚያስረሳ ፡ የይሁዳ ፡ አንበሳ

በምድር ፡ ያለ ፡ ሁሉ ፡ ቢጠራ ፡ ቢጠራ ፡ ለችግረኛ ፡ ሰው ፡ ምኑ ፡ ነው ፡ የሚራራ
ሞትህ ፡ ለኔ ፡ ይሁን ፡ እያለ ፡ ሰው ፡ ውሸቱን ፡ በስራ ፡ ያሳየ ፡ አግኝተናል ፡ አንዱን
ከመቃብር ፡ በላይ ፡ ፍቅሩን ፡ የገለጠ ፡ ቢጠቀስ ፡ አንድ ፡ የለም ፡ ከጌታ ፡ የበለጠ
ከጌታ ፡ የበለጠ (፪x)

አዝፍቅር ፡ እስከ ፡ መቃብር (፬x)
የስንቶች ፡ ፍቅር ፡ እስከ ፡ መቃብር
የኛ ፡ ግን ፡ ኢየሱስ ፡ የኛ ፡ ግን ፡ ኤልሻዳይ
የርሱ ፡ ፍቅር ፡ ያልፋል ፡ ከመቃብር ፡ በላይ
ፍቅር ፡ ያልፋል ፡ ከመቃብር (፬x)

በቁሙ ፡ የተጠላ ፡ የተኮራረፈ ፡ የሚዘጋበት ፡ በር
የሞቱ ፡ ቀን ፡ ደግሞ ፡ ያዙኝ ፡ ልቀቁኝ ፡ ሲል ፡ አብሮ ፡ ለመቀበር
መውደዱን ፡ ሲገልጽ ፡ በእንጉርጉሮ ፡ ዜማ ፡ አልቃሽ ፡ አስጠርቶ
የአርባው ፡ እለት ፡ ደግሞ ፡ ሙሾ ፡ ሲያወጣለት ፡ ሐውልት ፡ አሰርቶ

አቤት ፡ ሲዋደዱ ፡ ይላል ፡ ደግሞ ፡ ሌላው ፡ ነገሩ ፡ ያልገባው
ይደነቃል ፡ ብሎ ፡ የነዚህስ ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ እስከ ፡ መቃብር
አልሰማ ፡ የኔን ፡ ነገር ፡ ወዶኝ ፡ ስለሞተ ፡ ነፍሱን ፡ ስለሰጠ
የኔ ፡ ብርቱ ፡ አፍቃሪ ፡ ከመቃብር ፡ በላይ ፡ ሄዷል ፡ ወደሰማይ

በፍቅር ፡ እስራት ፡ ገመድ ፡ የገመደ ፡ ከሰው ፡ ጋር ፡ ሊወዳጅ ፡ ከላይ ፡ የወረደ
አብሮ ፡ ሄዶ ፡ ሄዶ ፡ ጫፍ ፡ እየደረሰ ፡ አይሰናበትም ፡ እየተመለሰ
ምድርና ፡ ሞላዋን ፡ ቢገለባብጠው ፡ ይምጣና ፡ ይወራረድ ፡ ጌታዬን ፡ አይበልጠው
ጌታዬን ፡ አይበልጠው (፪x)

አዝፍቅር ፡ እስከ ፡ መቃብር (፬x)
የስንቶች ፡ ፍቅር ፡ እስከ ፡ መቃብር
የኛ ፡ ግን ፡ ኢየሱስ ፡ የኛ ፡ ግን ፡ ኤልሻዳይ
የርሱ ፡ ፍቅር ፡ ያልፋል ፡ ከመቃብር ፡ በላይ
ፍቅር ፡ ያልፋል ፡ ከመቃብር (፬x)