From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ኢትዮጵያ ፡ ሃገሬ ፡ ኢትዮጵያ
መልካም ፡ እንዲሆንልሽ ፡ ዛሬ
ስሚልኝ ፡ ይህቺን ፡ ዝማሬ (፪x)
አምላክሽ ፡ እኮ ፡ ቀናተኛ ፡ ነው
ለሌላ ፡ አማልክት ፡ መስገድሽ ፡ ምነው
ለሱ ፡ ለአምላክሽ ፡ ብቻ ፡ ስገጂ
እጆችሽንም ፡ ወደእርሱ ፡ ዘርጊ
አዝ፦ ኢትዮጵያ (፬x)
ኢትዮጵያ ፡ እጆችሽን ፡ ወደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ዘርጊ
ኢትዮጵያ ፡ ኢትዮጵያ (፪x)
እርሱ ፡ እኮ ፡ ላንቺ ፡ መፍትሔ ፡ አለው
የሚጠራሽ ፡ ሊያሳርፍሽ ፡ ነው
ነይ ፡ ወደሱ ፡ ሸክምሽ ፡ ከብዷል
ተጠጊው ፡ እርሱን ፡ ያሳርፍሻል
አዝ፦ ኢትዮጵያ (፬x)
ኢትዮጵያ ፡ እጆችሽን ፡ ወደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ዘርጊ
ኢትዮጵያ ፡ ኢትዮጵያ (፪x)
ሊገነባሽ ፡ ነው ፡ በአዲስ ፡ ድንጋይ
ተነስቷል ፡ ባንቺ ፡ ኤልሻዳይ
አንቺም ፡ ተነሺ ፡ ተቀበይው
አምላኬ ፡ እንተ ፡ ውዴ ፡ ነህ ፡ በይው
አዝ፦ ኢትዮጵያ (፬x)
ኢትዮጵያ ፡ እጆችሽን ፡ ወደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ዘርጊ
ኢትዮጵያ ፡ ኢትዮጵያ (፪x)
ኢትዮጵያ ፡ ፈጥና ፡ እጆቿን ፡ ወደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ትዘረጋለች ፡ (አሜን)
ኢትዮጵያ ፡ ሃገሬ ፡ ኢትዮጵያ
መልካም ፡ እንዲሆንልሽ ፡ ዛሬ
ስሚልኝ ፡ ይህቺን ፡ ዝማሬ (፪x)
|