እንዳንተ ፡ ያለ (Endante Yale) - ሶፍያ ፡ ሽባባው

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሶፍያ ፡ ሽባባው
(Sofia Shibabaw)

Sofia Shibabaw 1.jpg


(1)

ፍቅር ፡ ከመቃብር ፡ በላይ
(Feqer Kemeqaber Belay)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፮ (2003)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 7:02
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሶፍያ ፡ ሽባባው ፡ አልበሞች
(Albums by Sofia Shibabaw)

ጌታ ፡ ሆይ ፡ በጐነትህንና ፡ ቸርነትህን ፡ መልካምነትህንና ፡ ፍቅርህን ፡ አይቼ
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ እንደሌለ ፡ ተረድቼ ፡ ልከተልህ ፡ ወሰንኩ


አዝ:- እግዚአብሔር ፡ እግዚአብሔር
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ኧረ ፡ ማን ፡ አለ (፪x)

በድዬና ፡ እጥፍቼ ፡ ሳለሁ ፡ ካንተ ፡ ርቄ (፪x)
በምህረት ፡ አየኸኝ ፡ እግዚአብሔር ፡ አምላኬ (፪x)
ምን ፡ አይነት ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ምክንያት ፡ የማይፈልግ (፪x)
እንዲሁ ፡ የሚያፈቅር ፡ በዳዩን ፡ የሚወድ (፪x)

አዝ:- መንፈስ ፡ ቅዱስ (፬x)
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ኧረ ፡ ማን ፡ አለ (፪x)

ኤሎሄ ፡ ኤሎሄ ፡ ላማ ፡ ሰበቅታኒ ፡ ብሎ ፡ ሞተ ፡ ለኛ
ለእኔ ፡ ብሎ ፡ ነው ፡ መቃብር ፡ የተኛ (፪x)

አዝ:- ኢየሱሴዋ (፬x)
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ኧረ ፡ ማን ፡ አለ (፪x)

ኧረ ፡ ማን ፡ አለ (፬x)