እድል ፡ ፋንታዬ (Edel Fantayie) - ሶፍያ ፡ ሽባባው

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሶፍያ ፡ ሽባባው
(Sofia Shibabaw)

Sofia Shibabaw 1.jpg


(1)

ፍቅር ፡ ከመቃብር ፡ በላይ
(Feqer Kemeqaber Belay)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፮ (2003)
ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 6:25
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሶፍያ ፡ ሽባባው ፡ አልበሞች
(Albums by Sofia Shibabaw)

እድል ፡ ፋንታዬ ፡ እግዚአብሔር (፪x)

ሰማያትን ፡ ጥሶ ፡ ህዋውን ፡ ሰንጥቆ
ከፀሐይ ፡ ሰባት ፡ እጅ ፡ ይልቅ ፡ አብረቅርቆ
ኦ ፡ ከማደሪያው ፡ መጣልኝ ፡ በማለዳ ፡ ፈለገኝ
በምህረቱ ፡ በራልኝ ፡ አብረቀረቀለኝ

አዝ፦ እድል ፡ ፋንታዬ ፡ እግዚአብሔር
የሌዊ ፡ አምላክ ፡ እግዚአብሔር
እድል ፡ ፋንታዬ ፡ ምስጋናዬ
የዳዊት ፡ አምላክ ፡ ዝማሬዬ (፪x)

ስትመርጥ ፡ አትከለከልም
አስታዋሽ ፡ እንዳንተ ፡ አላየሁም
ጌታዬ ፡ አንተኮ ፡ ልዩ ፡ ነህ
ለኔስ ፡ እድል ፡ ፋንታዬ ፡ ነህ (፪x)
(እድል ፡ ፋንታዬ ፡ እግዚአብሔር)

አዝ፦ እድል ፡ ፋንታዬ ፡ እግዚአብሔር
የሳሙኤል ፡ አምላክ ፡ እግዚአብሔር
እድል ፡ ፋንታዬ ፡ መኖሪያዬ
የዳንኤል ፡ አምላክ ፡ ዝማሬዬ/መመኪያዬ (፪x)

እድል ፡ ፋንታዬ ፡ እግዚአብሔር
እድል ፡ ፋንታዬ ፡ ምስጋናዬ
እድል ፡ ፋንታዬ ፡ መኖሪያዬ

እድሌን ፡ ከመረጥክ ፡ እንድሆን ፡ በፊትህ
ክብርህንም ፡ እንዳይ ፡ እንድዘምርልህ
አሜን ፡ አሜን ፡ እያልኩ ፡ እንበረከካለሁ
ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ እያልኩ ፡ እሰግድልሃለሁ

አዝ፦ እድል ፡ ፋንታዬ ፡ እግዚአብሔር
የሌዊ ፡ አምላክ ፡ እግዚአብሔር
እድል ፡ ፋንታዬ ፡ ምስጋናዬ
የዳዊት ፡ አምላክ ፡ ዝማሬዬ
እድል ፡ ፋንታዬ ፡ እግዚአብሔር
የሳሙኤል ፡ አምላክ ፡ እግዚአብሔር
እድል ፡ ፋንታዬ ፡ መኖሪያዬ
የዳንኤል ፡ አምላክ ፡ መመኪያዬ (፪x)

እድል ፡ ፋንታዬ ፡ እግዚአብሔር
እድል ፡ ፋንታዬ ፡ ምስጋናዬ
እድል ፡ ፋንታዬ ፡ እግዚአብሔር
እድል ፡ ፋንታዬ ፡ መኖሪያዬ