አላማዬ (Alamayie) - ሶፍያ ፡ ሽባባው

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሶፍያ ፡ ሽባባው
(Sofia Shibabaw)

Sofia Shibabaw 1.jpg


(1)

ፍቅር ፡ ከመቃብር ፡ በላይ
(Feqer Kemeqaber Belay)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፮ (2003)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 5:42
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሶፍያ ፡ ሽባባው ፡ አልበሞች
(Albums by Sofia Shibabaw)

አላማዬ ፡ አይደለም ፡ እራስን ፡ ማስከበር
አላማዬ ፡ አይደለም ፡ ለታይታ ፡ መቅረብ
አላማዬ ፡ አይደለም ፡ ከፍ ፡ ብሎ ፡ መታየት
አላማዬ ፡ አይደለም ፡ በዓለም ፡ ታዋቂነት

አዝ፦ አላማዬ ፡ ለመኖር ፡ ነው ፡ አስከብሬው ፡ ኢየሱሴን
አላማዬ (፬x)

ዋሽቶም ፡ ሰርቆም ፡ መስሎም ፡ አጭበርብሮም ፡ ሊያሸንፈው ፡ ይታገላል ፡ ኑሮን
ለሕሊናው ፡ ክስ ፡ ያስተባብላል ፡ ይሞታል ፡ ወይ ፡ ብሎ ፡ ያሳብባል
የሰው ፡ ጭንቀት ፡ ለመኖር ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ስለነገ ፡ ማሰብ ፡ ለከንቱ ፡ ነው
ነገ ፡ ይጨነቅ ፡ ስለራሱ ፡ ብሎ ፡ አላማ ፡ አለኝ ፡ ከሁሉ ፡ አስበልጦ

አላማዬ ፡ የከንቱ ፡ አይደለም
አላማዬ ፡ ታይቶ ፡ የሚጠፋ
አላማዬ ፡ ስራ ፡ ፈት ፡ አይደለም
አላማዬ ፡ አለኝ ፡ ብዙ ፡ ስራ

አዝ፦ አላማዬ ፡ ለመኖር ፡ ነው ፡ አስከብሬው ፡ ኢየሱሴን
አላማዬ (፬x)

አላማዬ ፡ አይደለም ፡ እራስን ፡ ማስከበር
አላማዬ ፡ አይደለም ፡ ለታይታ ፡ መቅረብ
አላማዬ ፡ አይደለም ፡ ከፍ ፡ ብሎ ፡ መታየት
አላማዬ ፡ አይደለም ፡ በዓለም ፡ ታዋቂነት

አዝ፦ አላማዬ ፡ ለመኖር ፡ ነው ፡ አስከብሬው ፡ ኢየሱሴን
አላማዬ (፬x)

እልፍን ፡ በእጁ ፡ ይዞ ፡ ወደኋላ ፡ የሚያይን ፡ ሰው ፡ አልሆንም ፡ ተላላ
ከእንግዲህ ፡ ቀኝ ፡ ኋላ ፡ ዞሬ ፡ አልሄድም ፡ አላማዬን ፡ አውቃለሁ ፡ የያዝኩትን
ኢየሱሴ ፡ ሁን ፡ የሞቴ ፡ ማምለጫ ፡ ተገደብኩኝ ፡ ከከንቱ ፡ እሩጫ
ፍቅር ፡ የሆነው ፡ የርሱ ፡ አላማ ፡ ስለገባት ፡ ነፍሴም ፡ አታቅማማ

አላማዬ ፡ የከንቱ ፡ አየደለም
አላማዬ ፡ ታይቶ ፡ የሚጠፋ
አላማዬ ፡ ስራ ፡ ፈት ፡ አይደለም
አላማዬ ፡ አለኝ ፡ ብዙ ፡ ስራ

አዝ፦ አላማዬ ፡ ለመኖር ፡ ነው ፡ አስከብሬው ፡ ኢየሱሴን
አላማዬ (፬x)
አላማዬ ፡ ለመኖር ፡ ነው ፡ አስከብሬው ፡ ኢየሱሴን
አላማዬ (፵x)