አምላኬ ክበርልኝ (አምላኬ ክበርልኝ) - ሶፍያ ሽባባ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሶፍያ ሽባባ
(Sofia Shibabaw)

Lyrics.jpg


(4)

አልበም
(አምላኬ ክበርልኝ)

ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሶፍያ ሽባባ ፡ አልበሞች
(Albums by Sofia Shibabaw)

አበቃላት ስባል ፈጽሞ ልረሳ
ከንፈር ሲመጡልኝ በዝቶብኝ አበሳ
ጣልቃ እየገባህ ነገሬን ስትለዋውጠው
ምርኮዬን በእጥፍ በብዙ ስትመልሰው
ሃይሌን ስታድስ ጉልበቴን ስታበረታ
ተባረክ እንጂ ሌላ ምን ልበልህ ጌታ

አምላኬ ክበርልኝ /3/
ሌላ ምን ምላሽ አለኝ
አምላኬ ንገስልኝ /3/
ሌላ ምን ምላሽ አለኝ

ባንተ አልኩኝ ኮራራ
ወጣሁት ትልቁን ተራራ
ሁሉን በጉልበትህ ችዬ
ላንተ ለመዘመር ታድዬ
በሃዘኑ መንፈስ ፈንታ
ደስታን አጠገብከኝ ጌታ
ሲገርመኝ እንባዬን ማበስህ
አፌን ደግሞ በሳቅ ሞላህ

አምላኬ ክበርልኝ /3/
ሌላ ምን ምላሽ አለኝ
አምላኬ ንገስልኝ /3/
ሌላ ምን ምላሽ አለኝ

ተነሳሁኝ እንደገና
ልደረድርልህ በገና
ይገባሃል የኔ ዝማሬ
ላንተ አይደለም ወይ መኖሬ
ውስጤ ይቃጠላልና
ሊናገር የአንተን ምስጋና
የማይበት ማዳንህን
ይኸው እንካ ምስጋናህን

አምላኬ ክበርልኝ /3/
ሌላ ምን ምላሽ አለኝ
አምላኬ ንገስልኝ /3/
ሌላ ምን ምላሽ አለኝ

እኔማ ታደያለሁ እኔማ
ደግ አባት አግኝቻለሁ እኔማ
እኔማ ታደያለሁ እኔማ
ማዳኑን አይቻለሁ እኔማ

አምላኬ ንገስልኝ /3/
ሌላ ምን ምላሽ አለኝ

ወጣሁ ከአለት ንቃቃት
ጥበት ጭንቀት ከሞላበት
ማዳንህን እንዳወራ
ታደከኝ ከዛ ከመከራ
የጠላቴ ፍላጎቱ
አልትሳካለትም ምኞቱ
በበቀል ቀባኸኝ እና
ከፍ አረከኝ እንደገና

አምላኬ/አባቴ/ጌታዬ ክበርልኝ /3/
ሌላ ምን ምላሽ አለኝ
አምላኬ/አባቴ/ጌታዬ ንገስልኝ /3/
ሌላ ምን ምላሽ አለኝ