ኤልሻዳይ ፡ ነው (Elshaday New) - ሲሳይ ፡ አበበ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሲሳይ ፡ አበበ
(Sisay Abebe)

Lyrics.jpg


(2)

ምንኛ ፡ ታጋሽ ፡ ነህ
(Menegna Tagash Neh)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2006)
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 6:25
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሲሳይ ፡ አበበ ፡ አልበሞች
(Albums by Sisay Abebe)

ኤልሻዳይ ነው እግዚአብሔር

ወዳእላዕፋት ወደ በኩራት ማህበር
እሱ ከመረጠኝ ክብሩን እንድናገር
ላመስግነው እንጂ ሌላ ምን እላለሁ
የወደደኝ ጌታን ከፍ አደርገዋለሁ

ጌታ ነው ልበለው ጌታ ነው ×2
ልዩ ነው ልበለው ልዩ ነው ×2

ኤልሻዳይ ነው እግዚአብሔር ×2
ኤልሻዳይ ነው እግዚአብሔር ×2
ገናና ነው እግዚአብሔር ×2
ገናና ነው እግዚአብሔር ×2

1.በባርነት ቀንበር ውስጥ ተጎሳቁዬ ሳለሁ
ከሞት መንገድ መልሶኝ በብርሀኑ ብርሀን አየሁ
አሁን ማንም አያውቀኝ በቀደመው ታሪኬ
በመስቀል ጠርቆታል የወደደኝ አምላኬ

ታሪኬም ኑሮዬም ተቀየረ በቃ ×2
ጠላቴ መሸበት ለኔ ሌቱ ነጋ ×2
ኤልሻዳይ ነው እግዚአብሔር ×2
ኤልሻዳይ ነው እግዚአብሔር ×2
ገናና ነው እግዚአብሔር ×2
ገናና ነው እግዚአብሔር ×2

2 .ፋሬስ ይሁን አለና አምላኬ አስጥሶኛል
ብዙ ኋለኛ ሳለሁ ፊተኛ አድርጎኛል
ስራዬን ሁሉ ሰርቶ ጎዳናዬን አቅንቷል
እግዚአብሔር መሐሪ ነው ፊቱን ለኔ አብርቷል

አዝማች .........

3. ሰው መሆኔ በእርሱ ነው ህይወቴም ያማረልኝ
ትቢያዬን ሁሉ አራግፎ ባለ ማዕረግ ያረገኝ
አላፍርበት ባወራው ጌታ የሰራልኝን
የከፋው ይክፋው እንጂ እግዚአብሔር ይክበርልኝ

ታሪኬም ኑሮዬም ተቀየረ በቃ ×2
ጠላቴ መሸበት ለኔ ሌቱ ነጋ ×2
ኤልሻዳይ ነው እግዚአብሔር
ኤልሻዳይ ነው እግዚአብሔር
ገናና ነው እግዚአብሔር
ገናና ነው እግዚአብሔር
አዶናይ ነው እግዚአብሔር
ሰላሜ ነው እግዚአብሔር
ሞገሴ ነው እግዚአብሔር
እረፍቴ ነው እግዚአብሔር