From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ ሞገሴ ፡ ነህ ፡ ኢየሱሴ (፪x)
የማልተካው ፡ የማልተወው ፡ በሕይወቴ
ማዕረጌ ፡ ነህ ፡ ኢየሱሴ ፡ የእኔ ፡ ኢየሱሴ
የማልተካው ፡ የማልተወው ፡ በሕይወቴ
ዛሬ ፡ ላየኝ ፡ ላስተዋለኝ ፡ ሰው
እኔ ፡ አልለውም ፡ እጄ ፡ አንዳረገው
እናገራለሁ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ብዬ
አልደብቀውም ፡ ኢየሱስዬን
እርሱ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ሞገስ ፡ የሆነኝ
ከአፈር ፡ አንስቶ ፡ ክብር ፡ ያሳየኝ
ታናሹን ፡ ሰው ፡ ሊያከብረኝ ፡ ወዶ
ቤቴ ፡ ገባ ፡ ከሰማይ ፡ ወርዶ
በዓይኖችህ ፡ ከታየሁኝ ፡ እኔ ፡ እጆችህ ፡ ከያዙኝ
ከዚህ ፡ ወዲያ ፡ በምን ፡ እሰጋለሁ
አንተን ፡ ይዣለሁ
አንተን ፡ ያስቀደመ ፡ ሰው
አይጐልም ፡ ከሚያስበው
ከዚህ ፡ ወዲያ ፡ በምን ፡ ይሰጋል
አንተን ፡ ይዞሃል
አዝ፦ ሞገሴ ፡ ነህ ፡ ኢየሱሴ (፪x)
የማልተካው ፡ የማልተወው ፡ በሕይወቴ
ማዕረጌ ፡ ነህ ፡ ኢየሱሴ ፡ የእኔ ፡ ኢየሱሴ
የማልተካው ፡ የማልተወው ፡ በሕይወቴ
ምሕረቱ ፡ የረዳው ፡ ሰው
ቸርነቱ ፡ ሰው ፡ ያረገው
እኔ ፡ ነኝ ፡ ያ ፡ ሰው ፡ እኔ ፡ ነኝ
በፍቅሩ ፡ የታደገኝ
አቅም ፡ አጣሁ ፡ ጉልበቴ ፡ ጠፋ
እኔስ ፡ የለኝም ፡ የመኖር ፡ ተስፋ
ብሎ ፡ ለሚል ፡ ጌታ ፡ አለው ፡ መላ
ታሪክ ፡ ከፍቶ ፡ ያሳያል ፡ ሌላ
በዓይኖችህ ፡ ከታየሁኝ ፡ እኔ ፡ እጆችህ ፡ ከያዙኝ
ከዚህ ፡ ወዲያ ፡ በምን ፡ እሰጋለሁ
አንተን ፡ ይዣለሁ
አንተን ፡ ያስቀደመ ፡ ሰው
አይጐልም ፡ ከሚያስበው
ከዚህ ፡ ወዲያ ፡ በምን ፡ ይሰጋል
አንተን ፡ ይዞሃል
አዝ፦ ሞገሴ ፡ ነህ ፡ ኢየሱሴ (፪x)
የማልተካው ፡ የማልተወው ፡ በሕይወቴ
ማረጌ ፡ ነህ ፡ ኢየሱሴ
የእኔ ፡ ኢየሱሴ
የማልተካው ፡ የማልተወው ፡ በሕይወቴ
|