ማራናታ (Maranatha) - ሰናይት ፡ እንግዳ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሰናይት ፡ እንግዳ
(Senait Engeda)

Lyrics.jpg


(3)

ኢየሱስ ፡ ትክክል
(Eyesus Tekekel)

ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 6:00
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሰናይት ፡ እንግዳ ፡ አልበሞች
(Albums by Senait Engeda)

አዝ፦ ለአንተ ፡ የሚሳንህ ፡ መቼም ፡ የለምና
የድንጋይ ፡ ልብን ፡ የሥጋ ፡ አድርግና
በምህረት ፡ ዓይንህ ፡ ተመልከተንና
ከዚህ ፡ ዓለም ፡ አላቀን ፡ ኢየሱስ ፡ ቶሎ ፡ ና
ማራናታ ፡ ጌታ ፡ ቶሎ ፡ ና
ከዚህ ፡ ዓለም ፡ አላቀን ፡ ኢየሱስ ፡ ቶሎ ፡ ና
ማራናታ ፡ ጌታ ፡ ቶሎ ፡ ና (፪x)

ስለኃጢአቱ ፡ የሞትክለት ፡ ህዝብ
በዚህ ፡ ዓለም ፡ ገዚ ፡ ልቡ ፡ ተያዘልህ
አንተ ፡ በቀጭኑ ፡ መንገድ ፡ ኑ ፡ ትላለህ
ህዝብህ ፡ ግን ፡ በሰፊው ፡ ገብቶ ፡ አለቀልህ
መልሰው ፡ ጌታ ፡ ቶሎ ፡ ናለት
 
አዝ፦ ለአንተ ፡ የሚሳንህ ፡ መቼም ፡ የለምና
የድንጋይ ፡ ልብን ፡ የሥጋ ፡ አድርግና
በምህረት ፡ ዓይንህ ፡ ተመልከተንና
ከዚህ ፡ ዓለም ፡ አላቀን ፡ ኢየሱስ ፡ ቶሎ ፡ ና
ማራናታ ፡ ጌታ ፡ ቶሎ ፡ ና (፪x)

ክብርህን ፡ በመተው ፡ እራህን ፡ አዋርደህ
ሥጋ ፡ በመልበስ ፡ በምድር ፡ ተንከራተህ
የሞትክለት ፡ ህዝብህ ፡ ኃይሉ ፡ ትጨፍኗል
ማስተዋሉ ፡ ጠፍቶ ፡ ልቡ ፡ ተተብትቧል
ጐብኚ ፡ አንተ ፡ ነህና ፡ ኢየሱስ ፡ ጐብኘን ፡ ይላል

አዝ፦ ለአንተ ፡ የሚሳንህ ፡ መቼም ፡ የለምና
የድንጋይ ፡ ልብን ፡ የሥጋ ፡ አድርግና
በምህረት ፡ ዓይንህ ፡ ተመልከተንና
ከዚህ ፡ ዓለም ፡ አላቀን ፡ ኢየሱስ ፡ ቶሎ ፡ ና
ማራናታ ፡ ጌታ ፡ ቶሎ ፡ ና (፪x)

ለአባቶቻችን ፡ እንደረዳሃቻው
ከግብጽ ፡ ባርነት ፡ እንዳወጣሃቸው
እንዳወረስካቻው ፡ የተስፋውን ፡ ቦታ
እኛም ፡ ከዚህ ፡ ዓለም ፡ ገዢም ፡ ሥር
እንፈታ ፡ ጐብኘን ፡ ጌታ

አዝ፦ ለአንተ ፡ የሚሳንህ ፡ መቼም ፡ የለምና
የድንጋይ ፡ ልብን ፡ የሥጋ ፡ አድርግና
በምህረት ፡ ዓይንህ ፡ ተመልከተንና
ከዚህ ፡ ዓለም ፡ አላቀን ፡ ኢየሱስ ፡ ቶሎ ፡ ና
ማራናታ ፡ ጌታ ፡ ቶሎ ፡ ና (፪x)

ከአንበሶች ፡ ጉድጓድ ፡ የሚያወጣው ፡ ኃይልህ
ከእሳት ፡ ነበልባል ፡ የሚያወጣው ፡ ክንድህ
ዛሬም ፡ በእኛ ፡ ዘመን ፡ እባክህ ፡ ይዘርጋ
ህዝብህን ፡ አድነው ፡ ከሰይጣን ፡ መንጋጋ
እኛን ፡ እርዳን ፡ እንድንተጋ

አዝ፦ ለአንተ ፡ የሚሳንህ ፡ መቼም ፡ የለምና
የድንጋይ ፡ ልብን ፡ የሥጋ ፡ አድርግና
በምህረት ፡ ዓይንህ ፡ ተመልከተንና
ከዚህ ፡ ዓለም ፡ አላቀን ፡ ኢየሱስ ፡ ቶሎ ፡ ና
ማራናታ ፡ ጌታ ፡ ቶሎ ፡ ና (፪x)