ክበር ፡ ተመስገን (Keber Temesgen) - ሰናይት ፡ እንግዳ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሰናይት ፡ እንግዳ
(Senait Engeda)

Lyrics.jpg


(3)

ኢየሱስ ፡ ትክክል
(Eyesus Tekekel)

ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 4:17
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሰናይት ፡ እንግዳ ፡ አልበሞች
(Albums by Senait Engeda)

ዐይኔ ፡ በማየቱ ፡ አንተን ፡ ያደንቅሃል
ጆሮዬ ፡ በመስማቱ ፡ ከፍ ፡ ያደርግሃል
ነፍስ ፡ መንፈስ ፡ ሥጋዬ ፡ አንተን ፡ ሾመውሃል
ተስማምተው ፡ ኢየሱስ ፡ ይግዛን ፡ ብለውሃል

አዝ፦ ክበር ፡ ተመስገን ፡ ክበር (፪x) ፡ እግዚአብሔር
ክበር ፡ ተመስገን ፡ ንገሥ (፪x) ፡ ጌታ ፡ እየሱስ

አበቦች ፡ ፈንድቁ ፡ እንሰሶች ፡ ዝለሉ
ዛፎች ፡ አሸብሽቡ ፡ አእዋፍ ፡ ዘምሩ
አዲስ ፡ ምሥጋና ፡ አምጡ ፡ አሜን ፡ ዕልል ፡ በሉ
በፊቱ ፡ ስገዱ ፡ ፍጥረታት ፡ በሙሉ

አዝ፦ ክበር ፡ ተመስገን ፡ ክበር (፪x) ፡ እግዚአብሔር
ክበር ፡ ተመስገን ፡ ክበር ፡ ንገሥ ፡ መስፈስ ፡ ቅዱስ

ከበሮው ፡ ይመታ ፡ በገናው ፡ ይደርደር
መለከት ፡ ይነፋ ፡ እምቢልታው ፡ ይጨመር
ክራሩንም ፡ ቃኙት ፡ አዲስ ፡ ቅኔ ፡ መዝሙር
በእግዚአብሔር ፡ ምሥጋና ፡ ይሙላ ፡ ሰማይ ፡ ምድር

አዝ፦ ክበር ፡ ተመስገን ፡ ክበር (፪x) ፡ እግዚአብሔር
ክበር ፡ ተመስገን ፡ ንገሥ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ

ፏፏቴዎች ፡ ፈንጩ ፡ በአምላካችሁ ፡ ፊት
ጨረቃ ፡ ድመቂ ፡ ፍኩ ፡ ከዋክብት
ብቻውን ፡ ታምራት ፡ ድንቅ ፡ አድርጓልና
ዙፋኑን ፡ ይክበበው ፡ ክብርና ፡ ምሥጋና

አዝ፦ ክበር ፡ ተመስገን ፡ ክበር (፪x) ፡ እግዚአብሔር
ክበር ፡ ተመስገን ፡ ንገሥ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ
ክበር ፡ ተመስገን ፡ ንገሥ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ