From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ ኦ ፡ ሃገሬን ፡ አስባት ፡ ኢትዮጵያን ፡ አስባት
የተዘጋውን ፡ ደጅ ፡ ከፍተህ ፡ ጌታ/ኢየሱስ
ሰላም ፡ ለአንቺ ፡ ይሁን ፡ በላት (፪x)
እግዚአብሔር ፡ አስባት ፡ ጐብኛት ፡ ኢትዮጵያን
እማጸንሃለሁ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ አፍስሼ ፡ እንባዬን
እግዜአብሄር ፡ ነህ ፡ ለኛ ፡ መድህኒታችን
ስለ ፡ ሥምህ ፡ አስብ ፡ አባት ፡ ሆይ ፡ የተስፋ ፡ ቃልህን
አዝ፦ ኦ ፡ ሃገሬን ፡ አስባት ፡ ኢትዮጵያን ፡ አስባት
የተዘጋውን ፡ ደጅ ፡ ከፍተህ ፡ ጌታ
ሰላም ፡ ለአንቺ ፡ ይሁን ፡ በላት (፪x)
ለልጅ ፡ ልጅ ፡ የሚተርፍ ፡ ቢኖር ፡ የአባት ፡ በደል
መሃሪ ፡ ነህና ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እባክህ ፡ ይቅር ፡ በል
መቅሰፍት ፡ ጉስቁልና ፡ ከእንግዲህስ ፡ ያብቃ
ከዙፋንህ ፡ ተነስ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ አንተ ፡ ግባ ፡ ጣልቃ
አዝ፦ ኦ ፡ ሃገሬን ፡ አስባት ፡ ኢትዮጵያን ፡ አስባት
የተዘጋውን ፡ ደጅ ፡ ከፍተህ ፡ ኢየሱስ
ሰላም ፡ ለአንቺ ፡ ይሁን ፡ በላት
እጁዋን ፡ አንስታለች ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ከፍ ፡ አድርጋ
መፍትሄ ፡ ሚገኘው ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ነውና ፡ ከአንተ ፡ ጋ
ወንዶችና ፡ ሴቶች ፡ ትልቅ ፡ ትንሾችም
እንለምንሃለን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ወድቀን ፡ በእግርህ ፡ ታች
አዝ፦ ኦ ፡ ሃገሬን ፡ አስባት ፡ ኢትዮጵያን ፡ አስባት
የተዘጋውን ፡ ደጅ ፡ ከፍተህ ፡ ጌታ
ሰላም ፡ ለአንቺ ፡ ይሁን ፡ በላት
ለምድራችን ፡ ከአንተ ፡ ፍቅር ፡ ሰላም ፡ ይምጣ
በዲያቢሎስም ፡ ላይ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ተነሳ ፡ በቁጣ
ሰማይ ፡ ይከፈት ፡ በረከትህ ፡ ይምጣ
የተጠማው ፡ ህዝብህ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ጠጥቶ ፡ እንዲረካ
አዝ፦ ኦ ፡ ሃገሬን ፡ አስባት ፡ ኢትዮጵያን ፡ አስባት
የተዘጋውን ፡ ደጅ ፡ ከፍተህ ፡ ጌታ/ኢየሱስ
ሰላም ፡ ለአንቺ ፡ ይሁን ፡ በላት (፪x)
|