ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ምርጫዬ (Eyesus New Merchayie) - ሰናይት ፡ እንግዳ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሰናይት ፡ እንግዳ
(Senait Engeda)

Lyrics.jpg


(3)

ኢየሱስ ፡ ትክክል
(Eyesus Tekekel)

ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 5:18
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሰናይት ፡ እንግዳ ፡ አልበሞች
(Albums by Senait Engeda)

አዝ፦ ለእኔስ ፡ አዳኜ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ምርጫዬ
የልብ ፡ ወዳጄ ፡ የእውነት ፡ የእውነት
የእውነት ፡ አፍቃሪዬ (፪x)

እናት ፡ ልጇን ፡ በጣር ፡ ትወልዳለች
ወልዳ ፡ ጡት ፡ አጥብታ ፡ ታሳድጋለች
በነፍሷ ፡ ላይ ፡ ድንገት ፡ ችግር ፡ ሲመጣ
ወንዝ ፡ ውስጥ ፡ ጣለችው ፡ ሙሴን ፡ አውጥታ
ግን ፡ አምላኩ ፡ እግዚአብሔር ፡ ሰበሰበው
በንጉሡ ፡ ቤት ፡ በተዓምር ፡ አሳደገው [1]
ለሞት ፡ የተሰጠውን ፡ አነሳና
በህዝቡ ፡ ላይ ፡ ሾመው ፡ ፀጋ ፡ አበዛና [2]

አዝ፦ ለእኔስ ፡ አዳኜ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ምርጫዬ
የልብ ፡ ወዳጄ ፡ የእውነት ፡ የእውነት
የእውነት ፡ አፍቃሪዬ

አጋር ፡ በምድረ ፡ በዳ ፡ ተሰደደች
አባት ፡ በልጁ ፡ ሲጨክን ፡ አየች
ውኃም ፡ አለቀ ፡ ምንዎን ፡ ታጠጣው
ጨነቃትና ፡ እራቀች ፡ ጥላው
ግን ፡ እግዚአብሔር ፡ ፈጥኖ ፡ መጣላት
ውሃውን ፡ አየች ፡ ዓይኗን ፡ ከፍቶላት
የሚያያትንም ፡ አየችውና
ቤቷ ፡ መለሳት ፡ ተስፋ ፡ ሰጣትና [3]

አዝ፦ ለእኔስ ፡ አዳኜ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ምርጫዬ
የልብ ፡ ወዳጄ ፡ የእውነት ፡ የእውነት
የእውነት ፡ አፍቃሪዬ

ወንድምንም ፡ አየሁት ፡ ጉድጓድ ፡ ሲጥል
ለባርነትም ፡ ሲሸጥ ፡ ለባዕድ ፡ ወገን [4]
ጌታ ፡ ግን ፡ ከግዞት ፡ አወጣውና
በረከት ፡ ሆነ ፡ ዮሴፍ ፡ ነገሠና [5]

ከሞተ ፡ አራት ፡ ቀን ፡ ሆኖታል
አለችው ፡ እህቱ ፡ አሁንስ ፡ ሸቶአል
የኢየሱሴ ፡ ፍቅር ፡ መቸ ፡ ያሸተዋል
አላዛርን ፡ በድንቅ ፡ ከሞት ፡ ያስነሳዋል [6]

አዝ፦ ለእኔስ ፡ አዳኜ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ምርጫዬ
የልብ ፡ ወዳጄ ፡ የእውነት ፡ የእውነት
የእውነት ፡ አፍቃሪዬ

እዮብ ፡ በቁስል ፡ እጅግ ፡ ተመቶ
ሚስቱ ፡ እንኳን ፡ ጠልታው ፡ የሚቀርበው ፡ አጥቶ
ክደህ ፡ ሙት ፡ ብላ ፡ ስታስቸግረው
በሸክሙ ፡ ላይ ፡ ቀንበር ፡ ስትጭነው [7]
አምላኩ ፡ እግዚአብሔር ፡ ከተፍ ፡ አለለት
ምርኮውን ፡ በእጥፍ ፡ በእጥፍ ፡ መለሰለት [8]
ሁሉንም ፡ በተራው ፡ አየሁት ፡ ቃኘሁት
ግን ፡ ኢየሱሴን ፡ በልጦ ፡ አገኘሁት

አዝ፦ ለእኔስ ፡ አዳኜ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ምርጫዬ
የልብ ፡ ወዳጄ ፡ የእውነት ፡ የእውነት
የእውነት ፡ አፍቃሪዬ

  1. ዘጸዓት ፪ ፡ ፩ - ፲ (Exodus 2:1-10)
  2. ዘጸዓት ፫ ፡ ፩ - ፬ : ፲፱ (Exodus 3:1-4:19)
  3. ዘፍጥረት ፳፩ ፡ ፲፭ - ፲፱ (Genesis 21:15-19)
  4. ዘፍጥረት ፴፯ ፡ ፲፰ - ፴፮ (Genesis 37:18-36)
  5. ዘፍጥረት ፵፩ ፡ ፵፩ - ፵፯ ፡ ፳፮ (Genesis 41:41 - 47:26)
  6. ዮሐንስ ፲፩ ፡ ፲፯ - ፵፬ (John 11:17-44)
  7. እዮብ ፪ ፡ ፯ - ፱ (Job 2:7-9)
  8. እዮብ ፵፪ ፡ ፲ - ፲፯ (Job 42:10-17)