ፀጋው ፡ ይርዳኝ (Tsegaw Yirdagn) - ሰላም ደስታ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሰላም ደስታ
(Selam Desta)

Selam Desta 1.jpg


(1)

አልደራደርም
(Alederaderem)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፫ (2020)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 6:19
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሰላም ደስታ ፡ አልበሞች
(Albums by Selam Desta)

አብልጬ/አብዝቼ ፡ እንድወድህ
አብዝቼ/አብልጬ ፡ እንዳፈቅርህ
አንተን ፡ ከመካድ ፡ ይልቅ ፡ እራሴን ፡ እንድክድ

ፀጋህ ፡ ይርዳኝ ፡ ፀጋህ ፡ ይርዳኝ
እኔ ፡ እንኳን ፡ በአቅሜ ፡ እጅግ ፡ ደካማ ፡ ነኝ

ሞት ፡ ቢሆን ፡ እስራት ፡ አንተን ፡ ለሚያገኝህ
እኔ ፡ እራሴን ፡ እሰዋለሁ ፡ ከአንተ ፡ አይበልጥብኝም
ብሎ ፡ ፊትህ ፡ እንዳላለ ፡ በገረድ ፡ ፊት ፡ ካደህ
ፀጋህ/ኃይልህ ፡ ዳግም ፡ አቆመና ፡ ስለአንተ ፡ መስካሪ/ሰባኪ ፡ አረገው

ፀጋህ ፡ ይርዳኝ ፡ ፀጋህ ፡ ይርዳኝ
እኔ ፡ እንኳን ፡ በአቅሜ ፡ እጅግ ፡ ደካማ ፡ ነኝ

ብዙ ፡ ፍቅርን ፡ መግለጥ ፡ በአፌ ፡ መቻሌ
ለተግባር ፡ ፈጥኜ/ቸኩዬ ፡ ግን ፡ አንተን ፡ መካዴ
ከአንተ ፡ ያነሰን ፡ ነገር ፡ ማድነቄ ፡ ቀርቶ
እንድወድህ ፡ ፀጋህ ፡ ይርዳኝ ፡ አብዝቶ

ፀጋህ ፡ ይርዳኝ ፡ ፀጋህ ፡ ይርዳኝ
እኔ ፡ እንኳን ፡ በአቅሜ ፡ እጅግ ፡ ደካማ ፡ ነኝ

ውድህ ፡ ያረከኝን ፡ አንተን ፡ ውዴ ፡ እንዳደርግህ
ከነፍስህ/ከክብርህ ፡ በላይ ፡ የወደድከኝን ፡ እንድወድህ
ጸጋህ/ሀይልህ ፡ በረዳኝ ፡ መጠን ፡ እንድቀርብህ
እኔም ፡ እሻከሁ ፡ የእውነቴን ፡ ልወድህ/ልመስልህ

ፀጋህ ፡ ይርዳኝ ፡ ፀጋህ ፡ ይርዳኝ
እኔ ፡ እንኳን ፡ በአቅሜ ፡ እጅግ ፡ ደካማ ፡ ነኝ