ተመርጫለው (Temerechalew) - ሰላም ፡ ደስታ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሰላም ፡ ደስታ
(Selam Desta)

Selam Desta 1.jpg


(1)

አልደራደርም
(Alederaderem)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፫ (2020)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 3:47
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሰላም ፡ ደስታ ፡ አልበሞች
(Albums by Selam Desta)

ተመርጫለው ፡ እኔ
ተወድጃለው ፡ እኔ
ፀድቄአለው ፡ በእርሱ
እንድኖርለት ፡ ለእርሱ (፪x)

ፀጋው ፡ በእምነት ፡ አድኖኝ
ኢየሱስ ፡ ጽድቁን ፡ አልብሶኝ
ስለኔ ፡ በአብ ፡ ፊት ፡ ታይቶ
ፈጽሞታል ፡ ሥራዬን ፡ ጨርሶ (፪x)

ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ፀጋው ፡ አቁሞኛል
ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ምህረቱ ፡ አኑሮኛል
ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ቸርነቱ ፡ በዝቶልኛል
ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ለዚህ ፡ ጌታ ፡ ክብር ፡ ይገባዋል

ለዚህ ፡ ጌታ ፡ ክብር ፡ ይገባዋል
ለዚህ ፡ ጌታ ፡ ስግደት ፡ ይገባዋል
ለዚህ ፡ ጌታ ፡ ልዕልና ፡ ይገባዋል
ለዚህ ፡ ጌታ ፡ አምልኮ ፡ ይገባዋል

ገና ፡ ከፍጥረት ፡ በቁጣ ፡ ነበርኩኝ
በበደሌ ፡ ምክንያት ፡ ሙት ፡ የሆንኩኝ
በኃጢአቴ ፡ መብዛት ፡ ሙት ፡ የሆንኩኝ (፪x)

ግን ፡ በምህረቱ ፡ ባለጠጋ ፡ ስለሆነ
ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ሕይወትን ፡ ለእኔ ፡ አደለ
ግን ፡ በምህረቱ ፡ ባለጠጋ ፡ ስለሆነ
ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ሕይወትን ፡ ለእኔ ፡ እንኪ ፡ አለ

ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ፀጋው ፡ አቁሞኛል
ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ምህረቱ ፡ አኑሮኛል
ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ቸርነቱ ፡ በዝቶልኛል
ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ለዚህ ፡ ጌታ ፡ ክብር ፡ ይገባዋል

ለዚህ ፡ ጌታ ፡ ክብር ፡ ይገባዋል
ለዚህ ፡ ጌታ ፡ ስግደት ፡ ይገባዋል
ለዚህ ፡ ጌታ ፡ ልዕልና ፡ ይገባዋል
ለዚህ ፡ ጌታ ፡ አምልኮ ፡ ይገባዋል