From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
እርቆ ፡ ለጠፋ ፡ ድርሻውን ፡ ይዞ
ከአባቱ ፡ ቤት ፡ ኮብልሎ ፡ ወደ ፡ ምኞት ፡ ጉዞ
እጅግ ፡ ክፉን ፡ ቢያደርግ ፡ ቢሆን ፡ ተላላ
ነፍሱን ፡ አልጠቀመም ፡ ከፍቶታል ፡ በጣም
አንድ ፡ ቀን ፡ ሲመለስ ፡ ወደ ፡ ልቡ
ሀሳቡን ፡ ሰብስቦ ፡ ሲቃኝ ፡ አባቱን
ይኖር ፡ ነበረ ፡ በደስታ ፡
አሁን ፡ ግን ፡ ገብቶታል ፡ መሆኑ ፡ ጎስቋላ
እንደ ፡ ልጁ ፡ ባያየኝ ፡ እንኳን ፡ ልሁን ፡ እንደ ፡ ባሪያ
ብሎ ፡ ለወሰነ ፡ ለቆረጠ ፡ ጀግና
ገና ፡ ሳይገባ ፡ ወደ ፡ መንደሩ ፡
አባቱ ፡ አቀፈው ፡ በፍቅር ፡ እጁ/ልክ ፡ እንደበፊቱ
ና ፡ ና ፡ ና ፡ ጌታ ፡ ይወድሀል
ና ፡ ና ፡ ና ፡ ደጁ ፡ ላይ ፡ ቆሞ ፡ ይጠራሀል
ና ፡ ና ፡ ና ፡ ውዴ ፡ ይወድሀል
ና ፡ ና ፡ ና ፡ ደጁ ፡ ላይ ፡ ቆሞ ፡ ይጠራሀል
ሁሉ ፡ እንዲመለስ ፡ በንስሀ ፡ ወዶ ፡ ይታገሳል ፡ ጌታ
ዝምታው ፡ በኃጥያት ፡ አይደለም ፡ ማለት ፡ በርታ
ቀን ፡ እጅግ ፡ ሳይከፋ ፡ ሳይመጣ ፡ የጥፋት ፡ ውሀ
እንዳን ፡ በልጁ ፡ ግባ ፡ ወደ ፡ መርከቡ
መርከብ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ማምለጫ ፡ መርከብ
ወጀቡ ፡ ቢያልም ፡ ፍፁም ፡ አትሰጋበት
ና ፡ ና ፡ ና ፡ ጌታ ፡ ይወድሀል
ና ፡ ና ፡ ና ፡ ደጁ ፡ ላይ ፡ ቆሞ ፡ ይጠራሀል
ና ፡ ና ፡ ና ፡ ውዴ ፡ ይወድሀል
ና ፡ ና ፡ ና ፡ ደጁ ፡ ላይ ፡ ቆሞ ፡ ይጠራሀል
ቢጠላ ፡ እንጂ ፡ ሀጥያትን ፡ ኃጥያተኛን ፡ ከልቡ ፡ ይወዳል
ይሉት ፡ የለ ፡ ወይ ፡ ቀድሞም ፡ እርሱ ፡ ከአመጸኞች ፡ ጋር ፡ ይወዳጃል
መሪ ፡ አጥተው ፡ ለተበተኑ ፡ እውነተኛ ፡ እረኛ ፡ ነው
ይሰበስባል ፡ በፍቅር ፡ እጁ ፡ አቅፎ ፡ ያሞቃል ፡ በእቅፉ
|