From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ስለበደላችን ፡ ደቀቀ
ስለኃጥያታችን ፡ ቆሰለ
ስለመተላለፋችን ፡ ሞተ
በመገረፉ ፡ ቁስል ፡ ፈወሰን
በቀራኒዮው ፡ ስፍራ ፡ በመስቀል ፡ የሞተው
በእሾህ ፡ ሲጎነጉኑ ፡ ደሙ ፡ የፈሰሰው
በጦር ፡ ጎኑን ፡ ሲሉ ፡ በአለንጋ ፡ ሲልጡ
ዝም ፡ ማለቱ ፡ ለእኛ ፡ ነው ፡ መራራን ፡ ሲያጠጡ
ፍጹም ፡ አላፈረም ፡ እርቃኑን ፡ ሲታይ ፡ ሰለ ፡ እኛ ፡ ለአለም
ስሙ ፡ ይክበር ፡ ዘላለም ፡ ይንገስ ፡ ወልድ ፡ እግዚአብሄር
በእራስ ፡ ቅሉ ፡ መንደር ፡ የፈሰሰው ፡ ደሙ ፡ ንጹህ ፡ ነው
ያለዋኖስ ፡ ያለበጐች ፡ ደም ፡ የአለምን ፡ በደል ፡ ጠረገው
ደሙን ፡ ይዞ ፡ ገባ ፡ ወደ ፡ አባቱ ፡ አወረደ ፡ ከላይ ፡ ምሕረቱን
አመጻችን ፡ ሁሉ ፡ ተወግዶ ፡ ተቆጠረ ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ፅድቁ
ፍጹም ፡ አላፈረም ፡ እርቃኑን ፡ ሲታይ ፡ ሰለ ፡ እኛ ፡ ለአለም
ሥሙ ፡ ይክበር ፡ ዘላለም ፡ ይንገስ ፡ ወልድ ፡ እግዚአብሄር
እጅጉን ፡ በችንካር ፡ አጥብቀው ፡ ወጠሩ
ጀርባውን ፡ በጅራፍ ፡ እያቆሰሉ
የአለማት ፡ ፈጣሪን ፡ ያለእፍረት ፡ ቢንቁ
ጸሀይ ፡ እና ፡ ጨረቃ ፡ እርሱን ፡ አከበሩ
በምሕረቱ ፡ ነው ፡ ባለጠጋ
እኛን ፡ ሊምር ፡ ወደደ ፡ ጌታ
እኛን ፡ አለ ፡ ሩሃማ (፪x)
እኔን ፡ አለ ፡ ሩሃማ (፪x)
|