ፍቅር ፡ ነህ (Feqer Neh) - ሰላም ደስታ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሰላም ደስታ
(Selam Desta)

Selam Desta 1.jpg


(1)

አልደራደርም
(Alederaderem)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፫ (2020)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 6:11
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሰላም ደስታ ፡ አልበሞች
(Albums by Selam Desta)

እንደአንተ ፡ የወደደኝ ፡ ማነው
እንደአንተ ፡ ያፈቀረኝ ፡ ማነው
እንደአንተ ፡ ያቀረበኝ ፡ ማነው
የምክኒያት/የሰበበ ፡ ወጤት ፡ ያልሆነ ፡ ፍቅር/መውደድ ፡ ያለው ፡ ማነው
ኢየሱስ (፮x)

ፍቅር ፡ ነህ ፡ እውነተኛ
ወዳጅ ፡ ነህ ፡ እውነተኛ
አባት ፡ ነህ ፡ እውነተኛ
ከነፍስህ/ከእራስህ ፡ በላይ ፡ ወደኸኛል
ከክብርህ ፡ በላይ ፡ ወደኸኛል
ከስምህ ፡ በላይ ፡ ወደኸኛል
ከነፍስህ ፡ በላይ ፡ ወደኸኛል
ከእራስህ ፡ በላይ ፡ ወደኸኛል

የተናቀ ፡ እጅግም ፡ የተጠላ ፡ የህማም ፡ ሰው
ደዌንም ፡ እንደሚያውቅ ፡ ብዙ ፡ ፊቱን ፡ እንደሚሰውር
ገዢ ፡ ለሻጭ ፡ እንደሚገምት ፡ እንደበግ ፡ ዝም ፡ ያለው
ለእርድ ፡ እንደሚነዳ ፡ ጠቦት ፡ አፉን ፡ ያልከፈተ

ፍቅር ፡ ነህ ፡ እውነተኛ
ወዳጅ ፡ ነህ ፡ እውነተኛ
አባት ፡ ነህ ፡ እውነተኛ
ከነፍስህ/ከእራስህ ፡ በላይ ፡ ወደኸኛል
ከክብርህ ፡ በላይ ፡ ወደኸኛል
ከስምህ ፡ በላይ ፡ ወደኸኛል
ከነፍስህ ፡ በላይ ፡ ወደኸኛል
ከእራስህ ፡ በላይ ፡ ወደኸኛል

ከጥም ፡ ሊረኩ ፡ ከረሀባቸው ፡ ሊጠግቡ
ብዙዎች ፡ ይቀርባሉ ፡ ሲያጡ ፡ ይሸሻሉ
ያለ ፡ ሰበብ/ምክንያት ፡ ወዶ ፡ የቀረበኝ ፡ ማን ፡ አለ
የተጠማ ፡ መስለህ ፡ ጥሜን ፡ ያረካህ ፡ አንድ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ

ፍቅር ፡ ነህ ፡ እውነተኛ
ወዳጅ ፡ ነህ ፡ እውነተኛ
አባት ፡ ነህ ፡ እውነተኛ
ከነፍስህ/ከእራስህ ፡ በላይ ፡ ወደኸኛል
ከክብርህ ፡ በላይ ፡ ወደኸኛል
ከስምህ ፡ በላይ ፡ ወደኸኛል
ከነፍስህ ፡ በላይ ፡ ወደኸኛል
ከእራስህ ፡ በላይ ፡ ወደኸኛል