እሄዳለው (Ehiedalew) - ሰላም ደስታ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሰላም ደስታ
(Selam Desta)

Selam Desta 1.jpg


(1)

አልደራደርም
(Alederaderem)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፫ (2020)
ቁጥር (Track):

፲ ፫ (13)

ርዝመት (Len.): 5:24
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሰላም ደስታ ፡ አልበሞች
(Albums by Selam Desta)

እኔማ ፡ አለኝ ፡ ክብር (፪x)
እኔማ ፡ አለኝ ፡ አክሊል (፪x)

ለጽዮን ፡ ስብሰባ ፡ ተጠርቻለሁ
ስራው ፡ በእኔ ፡ ተቆጥሮ ፡ ትገቢያለሽ ፡ ተብያለሁ
ኩነኔ ፡ የለብኝም ፡ ከሳሼስ ፡ ማነው
እርሱ ፡ በደሙ ፡ አጽድቆ ፡ ልጁ ፡ ተብያለሁ

ከግብጽ ፡ ምድር ፡ ቢወጡ
ወደ ፡ ተስፋይቱ ፡ ምድር
ወደ ፡ ውቧ ፡ ከነዓን ፡ ቢጠሩ
ብዙዎቹ ፡ ቀሩ ፡ ምድረ-በዳ
ሳይደርሱ ፡ ሳይገቡ ፡ ከእርስታቸው/ከግባቸው ፡ ጋር

ያ ፡ ተስፋ ፡ ከፊቴ ፡ ካለው ፡ ጋራ ፡ ፍጹም ፡ አይወዳደር
የኔማ ፡ አዲሲቱ ፡ ነው ፡ እየሩሳሌም

በበጉ ፡ ቅኔ ፡ በሙሴ ፡ ዜማ
እዘምራለሁ ፡ ከመላዕክት ፡ ጋራ
ክበር ፡ ክበር ፡ እያልኩ ፡ ፊቱ ፡ እቆማለሁ
እርሱ ፡ ስለረዳኝ ፡ እኔ ፡ እዘምራለሁ

እሄዳለሁ ፡ ልዘምር ፡ ወደላይ ፡ ወደላይ
እጠራለሁ ፡ ልዘምር ፡ ወደላይ ፡ ወደላይ

ከእነ ፡ አብርሀም ፡ ጋራ ፡ ከእነ ፡ ይስሀቅ
ከእነ ፡ እስራኤል ፡ ጋራ ፡ ከእነ ፡ ቅዱሳን

እሄዳለሁ ፡ ልዘምር ፡ ወደላይ ፡ ወደላይ
እጠራለሁ ፡ ልዘምር ፡ ወደላይ ፡ ወደላይ