ደሙ (Demurely) - ሰላም ደስታ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሰላም ደስታ
(Selam Desta)

Selam Desta 1.jpg


(1)

አልደራደርም
(Alederaderem)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፫ (2020)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 4:44
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሰላም ደስታ ፡ አልበሞች
(Albums by Selam Desta)

ደሙ (፲፪x)
የክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ ደም ፡ ከኃጥያት ፡ ሁሉ ፡ ያነፃል
የልጁ ፡ የኢየሱስ ፡ ደም ፡ ከበደል ፡ ሁሉ ፡ ያጸድቃል
የክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ ደም ፡ ከኃጥያት ፡ ሁሉ ፡ ያነፃል
የልጁ ፡ የኢየሱስ ፡ ደም ፡ ከበደል ፡ ሁሉ ፡ ያጸድቃል
አሜን ፡ ያነፃል ፡ ያጸድቃል

በመላለሻ ፡ በአደባባይ
እርቃኑን ፡ ተሰቅሎ ፡ ለሰው ፡ ልጅ ፡ ሲታይ
በግፍ ፡ እየተገፋ ፡ ተራራን ፡ ነጎደ
በቀራኒዮ ፡ ስፍራ ፡ በመስቀል ፡ ሞተ
አይተው ፡ እንዳይወዱ ፡ ደም ፡ ግባት ፡ የለውም
እጅግ ፡ የተጠላ ፡ ቁስለኛ ፡ ነው
ታዲያ ፡ ይሄማ ፡ እንዴት ፡ መድሀኒት ፡ ይሆናል
ያለው ፡ ሁሉ ፡ ይስማ ፡ ደሙ ፡ ያነፃል

የክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ ደም ፡ ከኃጥያት ፡ ሁሉ ፡ ያነፃል
የልጁ ፡ የኢየሱስ ፡ ደም ፡ ከበደል ፡ ሁሉ ፡ ያጸድቃል
የክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ ደም ፡ ከኃጥያት ፡ ሁሉ ፡ ያነፃል
የልጁ ፡ የኢየሱስ ፡ ደም ፡ ከበደል ፡ ሁሉ ፡ ያጸድቃል
አሜን ፡ ያነፃል ፡ ያጸድቃል

እንደ ፡ አሮን ፡ ልጆች ፡ ክህነት ፡ እንደሌዊ ፡ ዘር ፡ ስርዐት
አይደለም ፡ የውዴ ፡ አይደለም ፡ የውዴ
የኮርማ ፡ እና ፡ የዋኖስን ፡ ደም
መች ፡ ይዞ ፡ ገባ ፡ እኔን ፡ ለማፅደቅ

ሥጋውን ፡ አንዴ ፡ አቅርቦ ፡ ዘላለም ፡ ያማረ
ደሙ ፡ ፈሰሰና ፡ ኃጥያቴ ፡ ተሻረ
በቀራኒዮ ፡ ሞቱ ፡ ዳግም ፡ ወለደና
አብን ፡ አባ ፡ አልኩት ፡ ልጅ ፡ ነሽ ፡ ተባልኩና

የክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ ደም ፡ ከኃጥያት ፡ ሁሉ ፡ ያነፃል
የልጁ ፡ የኢየሱስ ፡ ደም ፡ ከበደል ፡ ሁሉ ፡ ያጸድቃል
የክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ ደም ፡ ከኃጥያት ፡ ሁሉ ፡ ያነፃል
የልጁ ፡ የኢየሱስ ፡ ደም ፡ ከበደል ፡ ሁሉ ፡ ያጸድቃል
አሜን ፡ ያነፃል ፡ ያጸድቃል