በቂ ፡ ነው (Beqi New) - ሰላም ደስታ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሰላም ደስታ
(Selam Desta)

Selam Desta 1.jpg


(1)

አልደራደርም
(Alederaderem)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፫ (2020)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 4:22
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሰላም ደስታ ፡ አልበሞች
(Albums by Selam Desta)

በጣም ፡ የከበረ ፡ እጅግ ፡ ያየለ
ከወርቅ ፡ እንቁ ፡ ይልቅ ፡ የተሻለ
በፍፁም ፡ ድርድር ፡ አብ ፡ የማያውቅበትን
አንድያ ፡ ልጁን/ክንዱን ፡ ሰጠ ፡ ኢየሱስን

አዝበቂ ፡ ነው ፡ ከበቂም ፡ በላይ (፫x)
ለሰማይ ፡ ቢሉ ፡ ለምድሩም ፡ ሲሳይ

ስቀበለው ፡ ያኔ ፡ እንደግል ፡ አዳኝ
መዘገበው ፡ ስሜን ፡ በላይኛው ፡ ሰማይ
የቅዱሳን ፡ ተስፋ ፡ በረከቴ ፡ ሆኖኛል ፡
ቀረኝ ፡ የምለው ፡ የለም ፡ አብ ፡ ጨርሶ ፡ ባርኮኛል
ስቀበለው ፡ ያኔ ፡ እንደግል ፡ አዳኝ
መዘገበው ፡ ስሜን ፡ በላይኛው ፡ ሰማይ
የቅዱሳን ፡ ተስፋ ፡ ስጦታዬ ፡ ሆኖኛል
ቀረኝ ፡ የምለው ፡ የለም ፡ አብ ፡ ሁሉንም ፡ ሰጥቶኛል

ከዚህ ፡ በላይ ፡ ባርኮት ፡ ምናለ ፡ ከዚህ ፡ በላይ ፡ በላይ
ከዚህ ፡ በላይ ፡ ደስታስ ፡ ምናለ ፡ ከዚህ ፡ በላይ ፡ በላይ
ከዚህ ፡ በላይ ፡ ሰላም ፡ ምናለ ፡ ከዚህ ፡ በላይ ፡ በላይ
አለም ፡ የሌላትን ፡ አገኘሁ ፡ ከላይ ፡ ከሰማይ

ዓሣ ፡ በምድር/በየብስ ፡ ላይ ፡ ሕይወት ፡ አያምረው
ከባህር ፡ እርቆ ፡ መኖር ፡ አያሰኘው
ሁልግዜ ፡ መገኛው ፡ አንድ ፡ እና ፡ አንድ ፡ ነው
ከውሀ ፡ የወጣ ፡ እለት ፡ መሞቻው ፡ ቅርብ ፡ ነው

የእኔም ፡ ያለኢየሱስ ፡ ልክ ፡ እንዲህ ፡ ባዶ ፡ ነው
ከመገኛ ፡ እርቆ ፡ መኖር ፡ ኧረ ፡ እንዴት ፡ ከንቱ ፡ ነው
የሕይወት ፡ እንጀራ ፡ ጠግቤ ፡ የሕይወት ፡ ውሀ ፡ ረክቼ
ከእርሱ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁ
መገኛዬ ፡ አንድ ፡ እና ፡ አንድ ፡ ነው
በረከቴ ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው

አዝበቂ ፡ ነው ፡ ከበቂም ፡ በላይ (፫x)
ለሰማይ ፡ ቢሉ ፡ ለምድሩም ፡ ሲሳይ