አቤቱ (Abietu) - ሰላም ደስታ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሰላም ደስታ
(Selam Desta)

Selam Desta 1.jpg


(1)

አልደራደርም
(Alederaderem)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፫ (2020)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 4:54
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሰላም ደስታ ፡ አልበሞች
(Albums by Selam Desta)

ምን ፡ አቃተህና ፡ ማህተሙን ፡ ፈትተሀል
ሰባቱን ፡ ጥቅል ፡ መጽሐፍ ፡ ልትከፍት ፡ ችለሀል
እንቆቅልሽ ፡ ፈቺ ፡ በማደሪያህ ፡ አለህ
በዙፋን ፡ ላይ ፡ ሆነህ ፡ ሁሉን ፡ ታድሳለህ

አቤቱ ፡ ውበትህን ፡ ማን ፡ ይመዝነዋል
የዳዊት ፡ ስር ፡ እና ፡ ዘር ፡ ስግደት ፡ ይገባሃል

በማደሪያህ ፡ ላይ ፡ አለህ/3
ሁሉን ፡ ታደርግ ፡ ዘንድ ፡ ቻይ ፡ ነህ
በችሎትህ ፡ ላይ ፡ አለህ/3
ሁሉን ፡ ታደርግ ፡ ዘንድ ፡ ቻይ ፡ ነህ

አልፋና ፡ ኦሜጋ ፡ ፊተኛ ፡ ኋለኛ
ጅማሬህ ፡ አይታወቅ ፡ ያንተ ፡ መጨረሻ
ገደብ ፡ ልክ ፡ የሌለህ ፡ ሀያል ፡ የእኛ ፡ ጌታ
በግርማ ፡ ሞገስህ ፡ ሁሉን ፡ የምትረታ

አቤቱ ፡ ውበትህን ፡ ማን ፡ ይመዝነዋል
የዳዊት ፡ ስር ፡ እና ፡ ዘር ፡ ስግደት ፡ ይገባሃል

የሞትና ፡ የሲኦል ፡ መክፈቻ ፡ በእጅህ ፡ ነው
በላይ ፡ ቢሆንም ፡ በታች ፡ ስልጣን ፡ ያንተ ፡ ነው
አዶናዩ ፡ ጌታ ፡ ምንስ ፡ ይሳንሀል
ቋጠሮውን ፡ ልትፈታ ፡ ብቻህን ፡ ችለሀል

አቤቱ ፡ ውበትህን ፡ ማን ፡ ይመዝነዋል
የዳዊት ፡ ስር ፡ እና ፡ ዘር ፡ ስግደት ፡ ይገባሃል

በማደሪያህ ፡ ላይ ፡ አለህ/3
ሁሉን ፡ ታደርግ ፡ ዘንድ ፡ ቻይ ፡ ነህ
በችሎትህ ፡ ላይ ፡ አለህ/3
ሁሉን ፡ ታደርግ ፡ ዘንድ ፡ ቻይ ፡ ነህ

በረከት ፡ እና ፡ ክብር ፡ ጥበብም ፡ ምስጋና
ለታረደው ፡ በግ ፡ ይሁን ፡ ለዚያ ፡ ለገናና
ሰቃይን ፡ እና ፡ ችግር ፡ መከራን ፡ ያስረሳ
ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ የይኁዳ ፡ አንበሳ

አቤቱ ፡ ውበትህን ፡ ማን ፡ ይመዝነዋል
የዳዊት ፡ ስር ፡ እና ፡ ዘር ፡ ስግደት ፡ ይገባሃል

በማደሪያህ ፡ ላይ ፡ አለህ (፫x)
ሁሉን ፡ ታደርግ ፡ ዘንድ ፡ ቻይ ፡ ነህ
በችሎትህ ፡ ላይ ፡ አለህ/3
ሁሉን ፡ ታደርግ ፡ ዘንድ ፡ ቻይ ፡ ነህ