እጠራዋለሁ (Eterawalew) - ሳሙኤል ፡ ንጉሤ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሳሙኤል ፡ ንጉሤ
(Samuel Negussie)

Lyrics.jpg


(2)

ኢየሱስ ፡ ዋናዬ ፡ ነው
(Eyesus Wanaye New)

ቁጥር (Track):

(2)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ንጉሤ ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Negussie)

እየሱስ የሚለው ስምህ
ልዩ ትርጉም አለው ለኔማ
ስጠራው ስደጋግመው

ጌታ እየሱስ የሚለው ስምህ
ልዩ ሰላም አለው ለኔማ
ስጠራው ስደጋግመው

እየሱስ የሚለው ስምህ
ልዩ ትርጉም አለው ለኔማ
ስጠራው ስደጋግመው

መፅናኛዬ ነው መበርቻዬ ነው ሆ
ከፍታዬ ነው መነሻዬ ነው ሆ
መፅናኛዬ ነው መበርቻዬ ነው ሆ
ከፍታዬ ነው ስሙ እየሱስ የሚለው

እጠራዋለው እጠራዋለው ይህን ስም
እጠራዋለው እጠራዋለው የሱሴን
እጠራዋለው እጠራዋለው ይህን ስም
ከሞት ያዳነኝን ህይወት የሰጠኝን የታደገኝን

ስንቱ ከሞት አመለጠ ስንቱ ከሞት ዳነ
ስንቱ የሃዘኑን ካባ ባንተ አውልቆ ጣለ
ስንቱ ከጨለማ እስራት በስምህ ተላቆ
ይኸው ይዘምርልሃል አደባባይ ቆሞ

በስምህ ውስጥ ሃይል አለ
በስምህ ውስጥ ስልጣን አለ
በስምህ ውስጥ መፍትሔ አለ
በእምነት ቆሞ እየሱስ ላለ
ስንቱን ተስፋ የቆረጠው ተስፋ ሆነህለት
ስንቱን አበቃ የተባለውን ህይወት ቀጠልክለት
ስንቱን ሞቱን የሚጠብቅ በጨለማ ሆኖ
ስንቱ በብርሃን ይኖራል ነገር ተገልብጦ

በስምህ ውስጥ ሃይል አለ
በስምህ ውስጥ ስልጣን አለ
በስምህ ውስጥ መፍትሔ አለ
በእምነት ቆሞ እየሱስ ላለ

በስምህ ውስጥ ሕይወት አለ
በስምህ ውስጥ መፍትሔ አለ
በስምህ ውስጥ ክብር አለ
በእምነት ቆሞ እየሱስ ላለ

እየሱሴ አንተን ደብቄ እንኳን ራሴን ላሳይ
እየሱሴ እንደው ባጋጣሚ ስምህን ሲያነሱ ሳይ
እየሱሴ እንባ ይቀድመኛል ምሆነውን አጣለሁ
እየሱሴ ፊቴ ድቅን ይላል የዋልክልኝ ሁሉ
እየሱሴ ክብርስ ቢሉ የቱ ክብሬ ነው
እየሱሴ ሁሉን ያገኘሁት ስምህን አምኜ ነው
እየሱሴ ቆሜ አደባባይ ገና አወራዋለሁ
እየሱሴ በስምህ አላፍርም አለም ሁሉ ይስማው

እጠራዋለው እጠራዋለው ይህን ስም
እጠራዋለው እጠራዋለው የሱሴን
እጠራዋለው እጠራዋለው ይህን ስም
ከሞት ያዳነኝን ህይወት የሰጠኝን የታደገኝን

በስምህ ውስጥ ሕይወት አለ
በስምህ ውስጥ መፍትሔ አለ
በስምህ ውስጥ ክብር አለ
በእምነት ቆሞ እየሱስ ላለ

እየሱሴ ስምህ መፍትሔ ነው ለጥየቄ ሁሉ
እየሱሴ ኧረ ማን አፍሯል በስምህ ተማምኖ
እየሱሴ የስምህም ጉልበት እኔም አውቀዋለሁ
እየሱሴ በስምህ ታምኜ ያለፍኩት ስንቱን ነው
እየሱሴ ለሞተው ነገር ህይወት የሰጠ
እየሱሴ ላበቃው ነገር ተስፋ የቀጠለ
እየሱሴ ብዙዎች ሲጠፉ በህይወት ያለሁት
እየሱሴ ታምኜው ነው ስምህን እዚ የደረስኩት

እጠራዋለው እጠራዋለው ይህን ስም
እጠራዋለው እጠራዋለው የሱሴን
እጠራዋለው እጠራዋለው ይህን ስም
ከሞት ያዳነኝን ህይወት የሰጠኝን የታደገኝን