ዙሪያዬን ፡ አላይም (Zuriyayien Alayem) - ሳሙኤል ፡ ንጉሤ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሳሙኤል ፡ ንጉሤ
(Samuel Negussie)

Samuel Negussie 1.jpg


(1)

BeEgziabhier Alem
(BeEgziabhier Alem)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፯ (2014)
ቁጥር (Track):

፲ ፬ (14)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ንጉሤ ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Negussie)

አልሰማም አልሰማም ሁኔታን አልሰማም
አልሰማም አልሰማም ነገሬን አልሰማም
አልሰማም አልሰማም ሰይጣንን አልሰማም
አልሰማም አልሰማም ሁኔታን አልሰማም

ዙሪያዬን አላይም የከበበኝን/3
ሁኔታን አልሰማም ሚያወራልኝን/3

በከበበኝ መሃል አሻግሬ አያለው
የተናገርከኝን እንደምትፈፅመው
በሁኔታው መሃል ድምፅህን እሰማለው
አባቴ ምትለው ትሻገራለህ ነው

ለዚ ነው ልቤ ያረፈው
ለዚ ነው ውስጤ ያረፈው
ለዚ ነው ሰላም የሞላኝ
ለዚ ነው ማልደነግጠው
ለዚ ነው ልቤ ያረፈው
ለዚ ነው ውስጤ ያረፈው
ለዚ ነው መረጋጋቴ
ለዚ ነው ደስታዬ የበዛው

ጠላት ጠፍቶ አይደለም የኔን ውድቀት ክፉ ሚሻ
ሰላም በዝቶ የምኖረው እንደዚ በደስታ
በባህር ላይ መንገድ በእሳት ውስጥ ማለፊያ አለው
ስለሆነ እንጂ አምላኬ እኔ የማመልከው

ከሚታየው ከሚሰማው በላይ አምነዋለው ታማኝ ነው የጠራኝ
ሁኔታውን አከባቢውን ትቼ ተደገፍኩኝ በቃ ልህ ወዳጄ

ለዚ ነው ልቤ ያረፈው
ለዚ ነው ውስጤ ያረፈው
ለዚ ነው መረጋጋቴ
ለዚ ነው ደስታዬ የበዛው

በማበል ወጀቡ ባውሎ ንፋስ ውስጥ ባልፍ እንኳን
ፈፅሞ አልፈራም እኔስ ስለሆነ ከኔ ጋር
በእምነቴ ፀናለው እጅ አልሰጥም ለሁኔታው
አውቃለሁ ከኔ ጋር የለው ከሁሉ በላይ ነው

ሌላ ሌላውን መስማቱን ትቻለው
የሱሴ አንተን ቃልህን ነው የማምነው
ሰማይ ምድር አገር ቢነዋወጥ
ኪዳን አለኝ ፍፁም ማይለወጥ

ዙሪያዬን አላይም የከበበኝን/3
ሁኔታን አልሰማም ሚያወራልኝን/3

በከበበኝ መሃል አሻግሬ አያለው
የተናገርከኝን እንደምትፈፅመው
በሁኔታው መሃል ድምፅህን እሰማለው
አባቴ ምትለው ትሻገራለህ ነው

ለዚ ነው ልቤ ያረፈው
ለዚ ነው ውስጤ ያረፈው
ለዚ ነው መረጋጋቴ
ለዚ ነው ደስታዬ የበዛው
ለዚ ነው ልቤ ያረፈው
ለዚ ነው ውስጤ ያረፈው
ለዚ ነው ሰላም የሞላኝ
ለዚ ነው ማልደነግጠው

አልሰማም አልሰማም ሁኔታን አልሰማም
አልሰማም አልሰማም ነገሬን አልሰማም
አልሰማም አልሰማም ሰይጣንን አልሰማም
አልሰማም አልሰማም ሁኔታን አልሰማም