From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
እንዴት እንዴት ይረሳል የዋልክልኛ
እንዴት እንዴት ይረሳል ያረክልኛ
የማይጠፋ ከልብ የማይረሳ ውለታ አለብኝ
የማይጠፋ ከልብ የማይወጣ ውለታ አለብኝ
የማይጠፋ ከልብ የማይረሳ ውለታ አለብኝ
የማይጠፋ ከልብ የፍቅር እዳ እኔስ አለብኝ
አመስግናልሁ እንደገና በአንተ በአንተ ታስቤአልሁና
አመስግናልሁ ደጋግሜ ምህርትህ ፍቅርህ ሰው አርጎኛል እኔን
የመኖሬ ምክነያት የሕይወቴ ዋና
የሰላሜ ምንጩ ኢየሱስ ላምልክህ እንደገና
የመቆሜ ምክንያት የሕይወቴ ዋና
የሰላሜ ምንጩ ኢየሱስ ላምልክህ እንደገና
የድሌን ብርሃን ሲፈነጥቅ ሰማይ አይረሳውም ልቤ አይረሳውም አይረሳውም አልዘነጋውም
ቀንዴ ከፍ ከፍ ሲል በጠላቶቼ ላይ አይረሳውም ልቤ አይረሳውም አይረሳውም አልዘነጋውም
ምክንይቴ ነህ አንተህ ይህን አውቃለሁ አይረሳውም ልቤ አይረሳውም አይረሳውም አልዘነጋውም
ለዚህ ያደረስከኝ ፍቅርህ እኮ ነው አይረሳውም ልቤ አይረሳውም አይረሳውም አልዘነጋውም
ኢየሱስ ትዝ ትዝ እያለኝ ትዝ ትዝ እያለኝ ሁሉም ያረክልኝ
ኢየሱስ በገናን አነሳው ደግሞ ልቀኝልህ መዘመር ጀመርኩኝ
ኢየሱስ የሕየወቴ ትርጉም የመኖሬ ዋና ባንተ ስለሆነ
ኢየሱስ ክማመስገን በቀር ላንተ የምሰጥው ሌላማ ምን አለኝ
አመስግናልሁ …>
አስጨናቂ ቀኖች ከእምነት የሚያጎሉ አይረሳውም ልቤ አይረሳውም አይረሳውም አልዘነጋውም
ሲሉኝ ሞኝንተ ነው ባንተ መታመኑ አይረሳውም ልቤ አይረሳውም አይረሳውም አልዘነጋውም
በፀጋ ደግፈህ አፅንተህ እንዳቆምከኝ አይረሳውም ልቤ አይረሳውም አይረሳውም አልዘነጋውም
መልካምነትህን ብዙ እንዳሳየኽኝ አይረሳውም ልቤ አይረሳውም አይረሳውም አልዘነጋውም
ኢየሱስ ትዝ ትዝ እያለኝ ...>
አመስግናልሁ ...>
|