From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
እግዚአብሔር ብርሃኔ መድሃኒቴ እኮ ነው/2
የሚያስደነግጠኝ የሚያስፈራኝ ማነው /2
ነገሬን በሙሉ በእጁ ይዞታል በእቅፉ ውስጥ ነው
ልቤ ማይፈራበት ዋስትናዬ እርሱ ነው ከለላዬ እርሱ ነው
ከለላዬ/8
መተማመኛዬ መተማመኛዬ
ልቤ ማይፈራበት ዋስታናዬ የነፍሴ አለኝታዬ
መተማመኛዬ መተማመኛዬ
ያንን ክፉ ዘመን ያለግኩብህ የነፍሴ አለኝታዬ
በልዑል መጠጊያ ከለላ የሚኖር
ሁሉን በሚችል ጥላ ውስጥ ያድራል ተማምኖ በእግዚአብሔር
ምህረት እንደ ጋሻ ሆኖለት ከለላ
እንዳባቶቹ ቃሉ እንደሚለው ይኖራል ሳይፈራ
አልሰግድም ብለው ላቆምከው ምስል ባንተ ተውራርደው
አምነውህ ገቡ ብርቱ እሳት ውስጥ ያድነናል ብለው
ቢነድ እሳቱ ቢያይል ፈተናው ሰባት እጥፍ ሆኖ
የታመኑበት የተደገፉት ከዚህም በላይ ነው
ሲጣሉ ሶስት ጠፍረው አስረው ወደቶን እሳት
ሲታዩ አራት ሲመላለሱ አለ አብሮ መላእክ
እንዴት ነው ታዲያ በቶን እሳት ውስጥ ዘና ወዲህ ወዲያ
እግዚአብሔር ያላው በእርሱ የታመነ እንደዚ ነው ለካ
ከለላዬ ነው/4
መመኪያዬ ነው/4
ከውሃ ፈሳሽ ዳር እንደተተከለ
ፍሬውን በየጊዜው እንደሚሰጥ እንደማያቆም
እኔም ከምንጩ ዳር ከእየሱስ ስለተጣበኩኝ
ክረምት ሆነ በጋ ስጋት የለም ሁሌ አፈራለሁኝ
ልምላሜ ነው ሁልጊዜ ማፍራት ስኖር ከየሱስ ጋር
ምንጩ ህያው ነው ይደርቃል ብዬ ፈፅሞም አልሰጋ
ሃምሳ መቶ እጥፍ አፈራለሁኝ በግንዱ ላይ ሆኜ
ለትውልድ ሁሉ በረከት ሚሆን ምንጭ አለ በህይወቴ
በድርቁ ዘመን ከቶ እንዳልሰጋ እንዳልጠወልግ
መልካም እረኛዬ ሁሌ ይመራኛል በእረፍት ወሃ ዘንድ
ምድረባዳውን ኤደን አድርጎ በረሃውን ገነት
በረሃቡ ዘመን ልቤ አይሰጋም ለምለም ነው የኔ ህይወት
ዋስትናዬ ነው/4
አለኝታዬ ነው/4
በረከቴ ነው/4
ፍሰሃዬ ነው/4
አልፈራም የነገው ህይወቴ አልፈራም በእጆችህ ተቃኝቷል
አልፈራም ከክብር ወደክብር አልፈራም ገና ይቀጥላል
አልፈራም ሹፈትን ቢያወራ አልፈራም ያክፉ ጠላቴ
አልፈራም በረከት ነው ብሏል አልፈራም የሰማዩ አባቴ
መመኪያዬ ነው/4
ደስታየ ነው/4
|