ሁልጊዜ ፡ መልካም (Hulgizie Melkam) - ሳሙኤል ፡ ንጉሤ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
Broom.png ይህ ፡ ጽሑፍ ፡ ገና ፡ አልተረጋገጠም ። እርማቶች ፡ ሊያስፈልጉት ፡ ይችላል ። ከቻሉ ፡ እርስዎ ፡ ያሻሽሉት
ሳሙኤል ፡ ንጉሤ
(Samuel Negussie)

Samuel Negussie 1.jpg


(1)

በእግዚአብሔር ፡ ዓለም
(BeEgziabhier Alem)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፯ (2014)
ቁጥር (Track):

(4)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ንጉሤ ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Negussie)

ሁልጊዜ መልካም ሁልጊዜ ፍቅር
ሁልጊዜ መልካም ሁልጊዜ ፍቅር
የማትለዋወጥ የማትቀየር የማትቀየር
የማትለዋወጥ የማትቀየር የማትቀየር
ወዳጄ አንተ ነህ ወዳጄ አንተ ነህ
ወዳጄ
የማትጥል የማትከዳ ሁልጊዜ አንተ ነህ ሁልጊዜ
ኢየሱስ አንተ ነህ
ኢየሱሴ አንተ ነህ
ኢየሱስ
የማትጥል የማትከዳ ሁልጊዜ አንተ ነህ ሁልጊዜ
መልካም ነህ ይህን አይቻለሁ
መልካም ነህ ሁሌ እናገራለሁ
ፍቅር ነህ ይህን አይቻለሁ
ፍቅር ነህ እመሰክራለሁ
አባት ነህ በቤትህ አድጌአለሁ
አባት ነህ ሁሌ እናገራለሁ
ደግ ነህ ከእጅህ በልቻለሁ
ደግ ነህ እንዴት እረሳለሁ
በጎውን ስጦታ
ፍፁም በረከትን ከላይ የሆነውን
እኔም አግኝቻለሁ
ከመልካምነትህ ከፍቅርህ ብርታት
ባሳለፍኩት ዘመን
አባቴ ልጅ ሆኜ ስኖር ካንተ ጋራ
ክፉ ሆነህ አታውቅም
ልቤ አቅም የለውም ይህንን ሊረሳ
መልካም ነህ ይህን አይቻለሁ
መልካም ነህ ሁሌ እናገራለሁ
ፍቅር ነህ ይህን አይቻለሁ
ፍቅር ነህ እመሰክራለሁ
አባት ነህ በቤትህ አድጌአለሁ
አባት ነህ ሁሌ እናገራለሁ
ደግ ነህ ከእጅህ በልቻለሁ
ደግ ነህ እንዴት እረሳለሁ
ከበግ እረኝነት
ደግሞ እሰከ ንግሥና ባለፈው ዘመን
ከጠጠር ከወንጭፍ
ከትንሹ ስፍራ እስከ ቤተ መንግስት
በሄደበት መንገድ
ብዙ የረዳኸው ፍቅርህን ያየ ሰው
ያመሰግንሃል
መልካም ነህ እያለ እንደኔ ያለው ሰው
እኔ ነኝ እኔ ነኝ እኔ ነኝ እኔ ነኝ
እኔ ነኝ እኔ ነኝ እኔ ነኝ እኔ ነኝ
 ምህረትህ የረዳኝ ፍቅርህ ያገዘኝ
አቤት አቤት ያሰው እኔ ነኝ
ብዙ የራራህልኝ ብዙ የደገፍከኝ
አዎ አዎ ያሰው እኔ ነኝ
ሁልጊዜ መልካም ሁልጊዜ ፍቅር
ሁልጊዜ መልካም ሁልጊዜ ፍቅር
የማትለዋወጥ የማትቀየር
መልካም ነህ ይህን አይቻለሁ
መልካም ነህ ሁሌ እናገራለሁ
ፍቅር ነህ ይህን አይቻለሁ
ፍቅር ነህ እመሰክራለሁ
አባት ነህ በቤትህ አድጌአለሁ
አባት ነህ ሁሌ እናገራለሁ
ደግ ነህ ከእጅህ በልቻለሁ
ደግ ነህ እንዴት እረሳለሁ