ኢየሱስ ፡ የሚለው ፡ ስም (Eyesus Yemilew Sem) - ሳሙኤል ፡ ንጉሤ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሳሙኤል ፡ ንጉሤ
(Samuel Negussie)

Samuel Negussie 1.jpg


(1)

በእግዚአብሔር ፡ ዓለም
(BeEgziabhier Alem)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፯ (2014)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 5:14
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ንጉሤ ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Negussie)

እየሱስ ፡ የሚለው ፡ ስምህ
ልዩ ፡ ትርጉም ፡ አለው ፡ ለእኔማ
ስጠራው ፡ ስደጋግመው (፪x)

መጽናኛዬ ፡ ነው ፡ መበርቻዬ ፡ ነው ፡ ሆ!
ከፍታዬ ፡ ነው ፡ መነሻዬ ፡ ነው ፡ ሆ!
መጽናኛዬ ፡ ነው ፡ መበርቻዬ ፡ ነው ፡ ሆ!
ከፍታዬ ፡ ነው ፡ ስሙ ፡ እየሱስ ፡ የሚለው

እጠራዋለው ፡ እጠራዋለው ፡ ይህን ፡ ስምህ
እጠራዋለው ፡ እጠራዋለው ፡ እየሱሴን
እጠራዋለው ፡ እጠራዋለው ፡ ይህን ፡ ስምህ
ከሞት ፡ ያዳነኝን ፡ ሕይወት ፡ የሰጠኝን ፡ የታደገኝን

እየሱስ ፡ እየሱስ ፡ እየሱስ ፡ እየሱስ (፬x)
በስምህ ፡ ውስጥ ፡ አለ ፡ ሰላም
በስምህ ፡ ውስጥ ፡ አለ
በስምህ ፡ ውስጥ ፡ አለ ፡ በረከት
በስምህ ፡ ውስጥ ፡ አለ
በስምህ ፡ ውስጥ ፡ አለ ፡ ኃይል
በስምህ ፡ ውስጥ ፡ አለ
እየሱስ ፡ እየሱስ ፡ በእምነት ፡ ላለ
ከሞት ፡ የሚያስጥል

(አንተን) ደብቄ ፡ እንኳን፡ ፡ እራሴን ፡ ላሳይ
(እየሱሴ) እንደው ፡ በአጋጣሚ ፡ ስምህን ፡ ሲያነሱ ፡ ሳይ
(እየሱሴ) እንባ ፡ ይቀድማኛል ፡ ምሆነውን ፡ አጣለሁ
(እየሱሴ) ፊቴ ፡ ድቅን ፡ ይላል ፡ ያረክልኝ ፡ ሁሉ
(እየሱሴ) ቆሜ ፡ አደባባይ ፡ ገና ፡ አወራዋለው
(እየሱሴ) በስምህ ፡ አላፍርም ፡ አለም ፡ ሁሉ ፡ ይስማው
(እየሱሴ) ክብርስ ፡ ቢሉ ፡ የቱ ፡ ክብሬ ፡ ነው
(እየሱሴ) ሁሉን ፡ ያገኘሁት ፡ ስምህን ፡ አምኜ ፡ ነው

እጠራዋለው ፡ እጠራዋለው ፡ ይህን ፡ ስምህ
እጠራዋለው ፡ እጠራዋለው ፡ እየሱሴን
እጠራዋለው ፡ እጠራዋለው ፡ ይህን ፡ ስምህ
ከሞት ፡ ያዳነኝን ፡ ሕይወት ፡ የሰጠኝን ፡ የታደገኝን

በስምህ ፡ ውስጥ ፡ አለ ፡ ሕይወት
በስምህ ፡ ውስጥ ፡ አለ
በስምህ ፡ ውስጥ ፡ አለ ፡ ክብር
በስምህ ፡ ውስጥ ፡ አለ
በስምህ ፡ ውስጥ ፡ አለ ፡ ስልጣን
በስምህ ፡ ውስጥ ፡ አለ
እየሱስ ፡ እየሱስ ፡ በእምነት ፡ ላለህ
ታሪክ ፡ የሚቀይር

ስምህ ፡ መፍትሄ ፡ ነው ፡ ለጥያቄ ፡ ሁሉ
(እየሱሴ) ኧረ ፡ ማን ፡ አፍሯል ፡ በስምህ ፡ ተማምኖ
(እየሱሴ) የስምን ፡ ጉልበት ፡ እኔም ፡ አውቀዋለው
(እየሱሴ) በስምህ ፡ ታምኜ ፡ ያለፍኩት ፡ ስንቱን ፡ ነው
(እየሱሴ) ለሞተው ፡ ነገር ፡ ሕይወት ፡ የሰጠህ
(እየሱሴ) ያበቃው ፡ ነገር ፡ ተስፋ ፡ እየቀጠለ
(እየሱሴ) ብዙዎች ፡ ሲጠፉ ፡ በሕይወት ፡ ያለሁት
(እየሱሴ) ታምኜው ፡ ነው ፡ ስምህን ፡ እዚህ ፡ የደረስኩት

እየሱስ ፡ እየሱስ ፡ ብዬ ፡ ስለው ፡ ብዬ ፡ ስለው
ሃይሌ ፡ ይታደሳል ፡ በረታለሁ ፡ በረታለሁ
እየሱስ ፡ እየሱስ ፡ ብዬ ፡ ስለው ፡ ብዬ ፡ ስለው
ከክብር ፡ ወደ ፡ ክብር ፡ እሻገራለሁ ፡ እጨምራለሁ