Samuel Negussie/BeEgziabhier Alem/Eyesus Anten Bemamenie

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
  የከፍታ ፡ ዘመን ፡ የብርሃን ፡ ሕይወት
  የሚጨምር ፡ ሰላም ፡ የሚጨምር ፡ ደስታ
  የክብር ፡ ዘመን ፡ ነው ፡ ከፊቴ ፡ ያለው
  መልካሙን ፡ አዋጅ ፡ እኔ ፡ አውጃለው
    ጨለማው ፡ አልፎ ፡ ያለቀስኩበት
    ዛሬ ፡ ብርሃን ፡ ሆንዋል ፡ 
    ኧረ ፡ በእኔስ ፡ ሕይወት
    አለም ፡ ሁሉ ፡ ይስማ
    ይህን ፡ ይወቅልኝ
    ምክንያቱም ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ 
    ኢየሱስ ፡ ስላለኝ
   ኢየሱስ አንተን ፡ በማመኔ (፫x)
   ኢየሱስ አንተን ፡ በማመኔ(፫x)
   ባርነቴ ፡ ቀርቶ ፡ ወራሽ ፡ ሆንኩ ፡ እኔ
   ወራሽ ፡ ሆኛለው ፡ ወራሽ ፡ ሆኛለው (፪x)
   ወራሽ ፡ ሆኛለው ፡ ወራሽ ፡ ሆኛለው ፡ አሄ
   ወራሽ ፡ ሆኛለሁ ፡ ልጅህ ፡ ሆኛለሁ
   ይኸው ፡ በደስታ ፡ አንተን ፡ አመልካለው
  ስላምና ደስታ ዕረፍት ሆነ ቤቴ
  መዳኔ ፡ ዕውን ፡ ሆነ ፡ ሳስገባው ወደ ቤቴ
  ነፃነቴን ፡ ላውጅ ፡ ከግዞት ፡ መውጣቴን
  በብርሃን ፡ አለም ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ መሆኔን
  ከእንግዲ ፡ ጨለማ ፡ በእኔ ፡ ሕይወት የለም
  ሞት ፡መውጊይው ተሰብርዋል እኔን አይነካኝም
  እርግማኔን ፡ ሽረህ ፡ ፅድቅን ፡ አለበስከኝ
  በማመኔ ፡ ብቻ ፡ ወራሽ ፡ አደረከኝ
   ኢየሱስ አንተን  በማመኔ (፫x)
   ኢየሱስ አንተን በማመኔ (፫x)
   ባርነቴ ቀርቶ ወራሽ ሆንኩ ፡ እኔ
   ይሁንልህ  ምሥጋና  ይሁንልህ  ዝማሬ
   ይሁንልህ  አምልኮ ይሁንልህ ጌታዬ (፪x)
  ከሞት ድኛለሁና  ከሞት  ድኛለሁና ከሞት
  ከሞት ድኛለሁና  ላንተ  ምስጋና
  የደም  ነው  ኪዳኑ  የተሳሰርንበት
  ከፍሎልኛል  ዋጋ  ያንድ ልጁን  ህይወት
  ሆኖኛል  አባቴ  እኔም  ደግሞ  ልጁ
  ወራሽ  አድርጎኛል  የሰማይ  የምድሩ
   የክብር  የከፍታ  የደስታ  መሆኑን
   አረጋግጫለው  የቀረው  ዘመኔን
   ድል  በነሳው  የሱስ  ድልን  ስላገኘው
   ከንግዲህ  ህይወቴ ላንተ መዘመር  ነው
   ባንተ  ታሰበ  የዘላለሜ ቀረ ባርነት 
   ነፃ  ሆንኩ  እኔ
   ዛሬ  በደስታ  እዘምራለው  
   የሰማይ  ዜጋ  ወራሽ  ሆኛለው
   ይሁንልህ ፡ ምስጋና ፡ ይሁንልህ ፡ ዝማሬ
   ይሁንልህ ፡ አምልኮ ፡ ይሁንልህ ፡ ጌታዬ
   ይሁንልህ ፡ ዕልልታ (፫x) 
   ይሁንልህ ፡ ለጌታ
    ከሞት ድኛለሁና ከሞት ድኛለሁና ከሞት
    ከሞት  ድኛለሁና ላንተ  ምስጋና
   
    ///////##///////##/////