እወድሃለሁ (Ewedehalehu) - ሳሙኤል ፡ ንጉሤ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሳሙኤል ፡ ንጉሤ
(Samuel Negussie)

Samuel Negussie 1.jpg


(1)

በእግዚአብሔር ፡ ዓለም
(BeEgziabhier Alem)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፯ (2014)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 7:23
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ንጉሤ ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Negussie)

የምወደው ፡ የምወደው ፡ ሁልግዜ
ደስ ፡ የሚለኝ ፡ ደስ ፡ የሚለኝ ፡ እኔስ ፡ ሁሌ (፪x)
ሳወራው ፡ ነው ፡ ሰው ፡ የመሆን ፡ ምክንያቴን
ሳወራው ፡ ነው ፡ የመዳኔን ፡ ምክንያቴን

ስለኔ ፡ በመስቀል ፡ ሞተሃል ፡ እወድሃለሁ ፡ እወድሃለሁ
ስለኔ ፡ ደምን ፡ አፍሥሰሃል ፡ እወድሃለሁ ፡ እወድሃለሁ
ስለኔ ፡ ያልሆንከው ፡ የቱ ፡ ነው ፡ እወድሃለሁ ፡ እወድሃለሁ
ምክንያትህ ፡ ለኔ ፡ ያለህ ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ እወድሃለሁ ፡ እወድሃለሁ

እወድሃለሁ ፡ እወድሃለሁ ፡ እንዳንተ ፡ ሚሆንልኝ ፡ ማነው
እወድሃለሁ ፡ እወድሃለሁ ፡ እየሱስ ፡ ታሪኬን ፡ ቀየርከው
እወድሃለሁ ፡ እወድሃለሁ ፡ እንዳንተ ፡ ሚያስብልኝ ፡ ማነው
እወድሃለሁ ፡ እወድሃለሁ ፡ ዘላለሜ ፡ ያማረው ፡ ባንተ ፡ ነው

ተስፋ ፡ ያልነበረውን ፡ ያንን ፡ ሂወቴን
የሞት ፡ ድምፅ ፡ ቢሰማ ፡ ጨለማው ፡ ቤቴ
በፍቅር ፡ ዘልቀህ ፡ ወደ ፡ ውስጠኛው ፡ ልቤ ፡ ውስጥ ፡ ገብተህ
አበራህልኝ ፡ የህይወቴን ፡ ብርሃን ፡ ተስፋህን ፡ ሰጠህ
ሰላምህ ፡ ህይወቴን ፡ አጥለቀለቀው
የደስታ ፡ ዘይት ፡ ውስጤን ፡ አራሰው
ዝምብዬ ፡ አይደለም ፡ በጥዋት ፡ ማታ ፡ እየሱስ ፡ የምለው
ፍቅርህ ፡ ታሪኬን ፡ ህይወት ፡ ዘመኔን ፡ መልካም ፡ አርጎት ፡ ነው

እወድሃለሁ ፡ እወድሃለሁ ፡ እንዳንተ ፡ የሚመቸኝ ፡ ማነው
እወድሃለሁ ፡ እወድሃለሁ ፡ እየሱስ ፡ ታሪኬን ፡ ቀየርከው
እወድሃለሁ ፡ እወድሃለሁ ፡ ዘላለሜ ፡ ያማረው ፡ ባንተ ፡ ነው
እወድሃለሁ ፡ እወድሃለሁ ፡ እንዳንተ ፡ ሚያስብልኝ ፡ ማነው

የምህረት ፡ ልብህ ፡ ለእኔ ፡ ያለህ
ሁሌ ፡ የሚፈልገኝ ፡ ማይሰለቸኝ ፡ ነህ
ምክንያቱ ፡ ሆነህ ፡ ከዘላለም ፡ ሞት ፡ ጥፋት ፡ መትረፌ
እንዲህ ፡ በሰላም ፡ እንዲህ ፡ በደስታ ፡ በህይወት ፡ መኖሬ
ወደድከኝ ፡ ወደድከኝ ፡ እስከሞት ፡ ድረስ
ተሰቃየህልኝ ፡ ህመሜን ፡ ታመምክ
ያን ፡ ሁሉ ፡ ስቃይ ፡ መራራን ፡ ፅዋ ፡ እንዲያ ፡ የጠጣኸው
ዛሬየን ፡ አይተህ ፡ በእረፍት ፡ እንድኖር ፡ ነው ፡ እወድሃለሁ

ለእኔ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ለእኔ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ዛሬዬን ፡ አይተህ ፡ ሁሉን ፡ ታገስከኝ ፡ እየሱስ ፡ ወዳጄ
ለእኔ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ለእኔ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ እወድሃለሁ ፡ ከሞት ፡ ያዳንከኝ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ውዴ

(መስከረም ፡ ጌቱ)
እወድሃለሁ ፡ እወድሃለሁ ፡ እንዳንተ ፡ ሚሆንልኝ ፡ ማነው
እወድሃለሁ ፡ እወድሃለሁ ፡ እየሱስ ፡ ታሪኬን ፡ ቀየርከው

እወድሃለሁ ፡ እወድሃለሁ ፡ እንዳንተ ፡ ሚራራልኝ ፡ ማነው
እወድሃለሁ ፡ እወድሃለሁ ፡ እንዳንተ ፡ የታገሰኝ ፡ ማነው
ሰላሜ ፡ ነህ ፡ ሰላሜ ፡ ነህ ፡ ሰላሜ
እረፍቴ ፡ ነህ ፡ እረፍቴ ፡ ነህ
በጣም ፡ የምወድህ ፡ በጣም ፡ የምወድህ