በረከቴ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (Bereketie Eyesus New) - ሳሙኤል ፡ ንጉሤ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሳሙኤል ፡ ንጉሤ
(Samuel Negussie)

Samuel Negussie 1.jpg


(1)

በእግዚአብሔር ፡ ዓለም
(BeEgziabhier Alem)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፯ (2014)
ቁጥር (Track):

(3)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ንጉሤ ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Negussie)

በስጋም ፡ በነፍስም ፡ የባረከኝ (፪x)
ደጋግሞ ፡ የባረከኝ
በልጁ ፡ በኢየሱስ ፡ የባረከኝ (፪x)
ደጋግሞ ፡ የባረከኝ
ጌታ ፡ አልበቃህም ፡ ወይ ፡ ባርከኽኝ (፪x)
እኔ ፡ እንኳን ፡ ብል ፡ በቃኝ
አንተ ፡ መቼ ፡ እረካህ ፡ ባርከኽኝ (፪x)
እኔ ፡ እንኳን ፡ ብል ፡ እፎይ
ሀዘን ፡ የሌለበት ፡ በረከት ፡ ደስታ ፡ ብቻ ፡ የሆነ
እየሱስን ፡ ሰጥተህ ፡ ባርከህኛል ፡ በል ፡ ሂድ ፡ ልጄ ፡ ብለህ
ሀዘን ፡ የሌለበት ፡ በረከት ፡ ደስታ ፡ ብቻ ፡ የሆነ
ኢየሱስን ፡ ሰጥተህ ፡ ባርከህኛል ፡ ተከናወን ፡ ብለህ
በረከቴ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ በረከቴ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፫x)
በረከቴ ፡ እራሱ ፡ ነው ፡ በረከቴ ፡ ማንነቱ ፡ ነው
አንዴ ፡ የሚወጣ ፡ ተመልሶ ፡ ደግሞ ፡ አንዴ ፡ የሚወርድ
አይደል ፡ በረከቴ ፡ በምድር ፡ እንዳለው ፡ የሚመጣ ፡ የሚሄድ
እየሱስን ፡ ሰጥተህ ፡ አንዴ ፡ ዘላለሜን ፡ አባ ፡ ባርከኽዋል
እጠቀመዋለው ፡ መንዝሬ ፡ መንዝሬ
እንኳን ፡ ለእኔ ፡ ለአለም ፡ ሁሉ ፡ ይበቃል
በረከቴ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ በረከቴ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፫x)
በረከቴ ፡ እራሱ ፡ ነው ፡ በረከቴ ፡ ማንነቱ ፡ ነው
በሰማዩ ፡ ስፍራ ፡ በመንፈሳዊ ፡ ሁሉ ፡ በረከት ፡ ባረከኝ
በልጁ ፡ በኢየሱስ ፡ ሥምም ፡ ስላመንኩኝ ፡ ሁሉን ፡ አወረሰኝ
የእርሱን ፡ በጐነት ፡ የእርሱን ፡ መልካምነት ፡ ለዓለም ፡ አወራለው
በረከቴ ፡ ኢየሱስ ፡ የጐደለኝ ፡ የለም ፡ አንተን ፡ ስላገኘው
የኔማ ፡ የኔማ ፡ በረከት ፡ ሰላም ፡ የሞላበት ፡ ደስታ ፡ የሞላበት
እየሱስ ፡ ያለበት
የእኔማ ፡ የእኔማ ፡ በረከት ፡ የተትረፈረፈ ፡ ፈጽሞ ፡ የማያልቅ
እየሱስ ፡ ያለበት
ኢየሱስ ፡ ያለበት (፯x)
ሰላም ፡ የሞላበት
ኢየሱስ ፡ ያለበት (፯x)
ኢየሱስ ፡ ያለበት
በረከቴ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ በረከቴ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፫x)
በረከቴ ፡ እራሱ ፡ ነው ፡ በረከቴ ፡ ማንነቱ ፡ ነው