From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
በዚህ ፡ ዓለም ፡ ምን ፡ ደስ ፡ የሚያሰኝ ፡ ነገር ፡ አለ
ከአንተ ፡ ጋር ፡ አንደመኖር
በዚህ ፡ ምድር ፡ ምን ፡ ደስ ፡ የሚያሰኝ ፡ ነገር ፡ አለ
ከአንተ ፡ ጋር ፡ አንደመኖር
እወደዋለሁ ፡ ሕይወቴን ፡ የለወጠው
እወደዋለሁ ፡ መኖሬን ፡ እወደዋለሁ
በአንተ ፡ ዘንድ ፡ ያለን ፡ የህይወት ፡ ቃል
ሌላ ፡ ስፍራ ፡ የትም ፡ ማላገኘው
ብር ፡ የማይሰጠኝ ፡ ወርቅ ፡ የማይሰጠኝ
የሕይወቴን ፡ አቅጣጫ ፡ የለወጠው
የሁልጊዜ ፡ ነው ፡ የልቤ ፡ ሰላም
ከመንፈስህ ፡ ከቃልህ ፡ የመነጨው
በዚህ ፡ አለም ፡ ነገር ፡ የማይወሰን
የእኔን ፡ ሕይወት ፡ የደስታ ፡ ያደረገው
ብዙ ፡ ደስታ ፡ አለ ፡ በሕይወቴ
ብዙ ፡ ሰላም ፡ አለ ፡ በሕይወቴ
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ስላለ
መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ በእኔ ፡ ውስጥ ፡ ስላለ
ሸክም ፡ የከበደው ፡ ወደ ፡ እኔ ፡ ይምጣ
ይረፍ ፡ ብለህ ፡ የጠራኸኝ ፡ አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ
ሁሉንም ፡ ነገር ፡ ለ ፡ አንተ ፡ ሰጥቼ
እፎይ ፡ ብዬ ፡ ተደላድዬ ፡ ምኖርብህ
ኢየሱስ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ያለኝ ፡ ህብረት
ማለት ፡ ለእኔ ፡ አለሜ ፡ ነው
ለሕይወቴ ፡ ትርጉም ፡ ያገኘሁበት
ምክኒያቱ ፡ ነው ፡ የዘላለሜ ፡ የሰመረበት
|