ይህች ፡ ቀን (Yehech Qen) - ሳሙኤል ፡ ካሳሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሳሙኤል ፡ ካሳሁን
(Samuel Kassahun)

Samuel Kassahun 1.png


(1)

ያልተሰማ
(Yaltesema)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2013)
ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 6:38
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ካሳሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Kassahun)

አዝ፦ ይህች ፡ ቀን ፡ ለእኔ ፡ ነች ፡ ጌታ ፡ የሰራት
ከሕግ ፡ ባርነት ፡ ነጻ ፡ ወጣሁባት (፪x)

አዲስን ፡ ምዕራፍ ፡ በእርሱ ፡ አየሁባት (፪x)
ተደላድዬ ፡ በእርሱ ፡ እኖራለሁ
ሌሎች ፡ የዘሩትን ፡ እኔ ፡ አጭዳለሁ
በተጠናቀቀው ፡ በእሱ ፡ እኖራለሁ

አዎ (፬x)

ፊደል ፡ ሕይወት ፡ አይሆን ፡ መንፈስ ፡ ካልመጣልኝ
በፀጋ ፡ ላይ ፡ ፀጋ ፡ ተትረፈረፈልኝ
መውደዱን ፡ ገለጸ ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ሞቶልኝ
መች ፡ ቃሉን ፡ ያጥፍና ፡ ተናግሮአል ፡ ጌታዬ

ኦሆ ፡ ለእኔ (፮x)

አዝ፦ ይህች ፡ ቀን ፡ ለእኔ ፡ ነች ፡ ጌታ ፡ የሰራት
ከሕግ ፡ ባርነት ፡ ነጻ ፡ ወጣሁባት (፪x)

ጌታ ፡ አሳርፎኛል ፡ ስራዬን ፡ ሰርቶልኝ
መቅበዝበዜ ፡ አበቃ ፡ ምንም ፡ አልጨምርም
አንድም ፡ አላስቀረም ፡ ሁሉን ፡ ፈጽሞልኝ
ከክርስቶስ ፡ ጋራ ፡ ወራሽ ፡ አደረገኝ
አደረገኝ (፪x)
ኦሆ ፡ እኔን ፡ ኦሆሆ ፡ እኔን (፪x)

አዝ፦ ይህች ፡ ቀን ፡ ለእኔ ፡ ነች ፡ ጌታ ፡ የሰራት
ከሕግ ፡ ባርነት ፡ ነጻ ፡ ወጣሁባት (፪x)

ጽድቄ ፡ ከእግዚኣብሔር ፡ ነው ፡ በነጻ ፡ ተሰጥቶኝ
ሚኮንነኝ ፡ ማነው ፡ እርሱ ፡ ከወደደኝ
ኃጢአት ፡ ተወገደ ፡ በጌታዬ ፡ በኢየሱስ
ሞት ፡ መውጊያው ፡ ተቀማ ፡ በሕይወት ፡ እንድነግስ
እንድነግስ
ኦሆ ፡ እንድነግስ ፡ ኦሆሆ ፡ እንድነግስ (፪x)

አዝ፦ ይህች ፡ ቀን ፡ ለእኔ ፡ ነች ፡ ጌታ ፡ የሰራት
ከሕግ ፡ ባርነት ፡ ነጻ ፡ ወጣሁባት (፪x)