ተብሎ ፡ ያላለቀ (Tebelo Yalaleqe) - ሳሙኤል ፡ ካሳሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሳሙኤል ፡ ካሳሁን
(Samuel Kassahun)

Samuel Kassahun 1.png

(1)

ያልተሰማ
(Yaltesema)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2013)
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 4:59
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ካሳሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Kassahun)

አዝ፦ ተብሎ ፡ ያላለቀ ፡ ተነግሮ ፡ ያልተሰማ
ለኔ ፡ ያለው ፡ የተሻለ ፡ አይን ፡ ያላየው ፡ የከበረ (፪x)
ተብሎ ፡ ያላለቀ ፡ ተነግሮ ፡ ያልተሰማ
ለኔ ፡ ያለው ፡ የተሻለ ፡ አይን ፡ ያላየው ፡ የከበረ (፪x)

ውዴ ፡ ያንተን ፡ ቃል ፡ ሰምቻለሁ
የናፈቅኩትን ፡ አግኝቼዋለሁ
ሃሳቤን ፡ የእኔን ፡ አስወግጄአለሁ
አንተ ፡ የእኔ ፡ ነህ ፡ አመልክሃለሁ (፫x)

አዝ፦ ተብሎ ፡ ያላለቀ ፡ ተነግሮ ፡ ያልተሰማ
ለኔ ፡ ያለው ፡ የተሻለ ፡ አይን ፡ ያላየው ፡ የከበረ (፪x)
ተብሎ ፡ ያላለቀ ፡ ተነግሮ ፡ ያልተሰማ
ለኔ ፡ ያለው ፡ የተሻለ ፡ አይን ፡ ያላየው ፡ የከበረ (፪x)

አንተን ፡ ለሚወዱ ፡ እንደ ፡ ሃሳብህ ፡ ለተጠሩ
ነገር ፡ ሁሉ ፡ ለበጎ ፡ ነው
እንዳሰብከው ፡ እንዳወቅከው

መታመን ፡ በአንተ ፡ ለእኔ ፡ ማትረፍ ፡ ነው
ቀድሞ ፡ ያየውን ፡ ነው ፡ የምኖረው
ስጋት ፡ ሳይገባኝ ፡ እራመዳለሁ
መልካም ፡ መልካም ፡ ነው ፡ ካንተ ፡ የሚፈልቀው
በቤትህ ፡ ሁሌ ፡ እዘምራለሁ
መልካም ፡ መልካም ፡ ነው ፡ ካንተ ፡ የሚፈልቀው

አዝ፦ ተብሎ ፡ ያላለቀ ፡ ተነግሮ ፡ ያልተሰማ
ለኔ ፡ ያለው ፡ የተሻለ ፡ አይን ፡ ያላየው ፡ የከበረ (፪x)
ተብሎ ፡ ያላለቀ ፡ ተነግሮ ፡ ያልተሰማ
ለኔ ፡ ያለው ፡ የተሻለ ፡ አይን ፡ ያላየው ፡ የከበረ (፪x)

ፍጻሜና ፡ ክብር ፡ የሞላበት ፡ ተስፋ
ነው ፡ ያቀረበልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ የእኛ ፡ ጌታ

ያልከው ፡ ሆነ
ሃሳብህ ፡ ተፈጸመ (፬x)