ስላንተ (Selante) - ሳሙኤል ፡ ካሳሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሳሙኤል ፡ ካሳሁን
(Samuel Kassahun)

Samuel Kassahun 1.png


(1)

ያልተሰማ
(Yaltesema)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2013)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 6:36
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ካሳሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Kassahun)

ቃልህን ፡ ሰምቼ ፡ ሥራህን ፡ አይቼ
አይኔ ፡ በርቶልኛል ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ
እዚህም ፡ እዚያም ፡ አልልም ፡ ለቅቄህ ፡ አልሄድም
በጥበቃህ ፡ ሥር ፡ ነኝ ፡ አልሻም ፡ ሌላውን (፫x)

ኦሆ

አዝ፦ ስላንተ ፡ ያወራሉ ፡ ሰው ፡ ሲናገር ፡ ስለሰሙ
የሰው ፡ ስርዓት ፡ ወግ ፡ ልማዱ ፡ ሕይወት ፡ የለሽ ፡ አምልኮውን
ኃይል ፡ ብርታቱን ፡ የከዳውን ፡ መች ፡ ሊገባኝ ፡ እርሱን ፡ ላየው
በእውነት ፡ ልስገድ ፡ ለሚገባው
ወደር ፡ መሳይ ፡ ለእኔ ፡ የለው
በእውነት ፡ ላክብር ፡ ስለምወደው

ኦሆ

ለደካማው ፡ ብርታት ፡ ለዛለውም ፡ ጉልበት
ማለምለምን ፡ ሚወድ ፡ ድንቅ ፡ መካር ፡ ሀያል ፡ ነው
የኢየሱስ ፡ ከኔ ፡ ጋር ፡ ነው ፡ ማንን ፡ እፈራለሁ
የሚያቆመኝ ፡ የለም ፡ ከፍ ፡ ብዬ ፡ እሄዳለሁ
እንደ ፡ ንስር ፡ እወጣለሁ
ከፍ ፡ ብዬ ፡ እሄዳለሁ

ኦሆ

አዝ፦ ስላንተ ፡ ያወራሉ ፡ ሰው ፡ ሲናገር ፡ ስለሰሙ
የሰው ፡ ስርዓት ፡ ወግ ፡ ልማዱ ፡ ሕይወት ፡ የለሽ ፡ አምልኮውን
ኃይል ፡ ብርታቱን ፡ የከዳውን ፡ መች ፡ ሊገባኝ ፡ እርሱን ፡ ላየው
በእውነት ፡ ልስገድ ፡ ለሚገባው
ወደር ፡ መሳይ ፡ ለእኔ ፡ የለው
በእውነት ፡ ላክብር ፡ ስለምወደው

ያማረ ፡ ዝማሬ ፡ ቅኔዬም ፡ ለእርሱ ፡ ነው
ሁሉ ፡ ከእርሱ ፡ በእርሱ ፡ ለእርሱ ፡ ነው ፡ የምሰጠው
በገና ፡ ልደርድር ፡ መሰንቆዬን ፡ ላንሳ
የከንፈሬን ፡ ፍሬ ፡ ዜማዬን ፡ ላሰማ
ምሥጋና ፡ ላሰማ ፡ ዜማዬን ፡ ላሰማ

አዝ፦ ስላንተ ፡ ያወራሉ ፡ ሰው ፡ ሲናገር ፡ ስለሰሙ
የሰው ፡ ስርዓት ፡ ወግ ፡ ልማዱ ፡ ሕይወት ፡ የለሽ ፡ አምልኮውን
ኃይል ፡ ብርታቱን ፡ የከዳውን ፡ መች ፡ ሊገባኝ ፡ እርሱን ፡ ላየው
በእውነት ፡ ልስገድ ፡ ለሚገባው
ወደር ፡ መሳይ ፡ ለእኔ ፡ የለው
በእውነት ፡ ላክብር ፡ ስለምወደው

ፍሬ ፡ የለሽ ፡ ከንቱ ፡ ወሬ ፡ መች ፡ ኣውቃለሁ
የአንተን ፡ ቃል ፡ በንፁህ ፡ ልብ ፡ እኔ ፡ አምናለሁ (፪x)