From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ ቅጥሬ ፡ መዳን ፡ ሆኖአል ፡ ጌታ
በሬ ፡ ምስጋና
ነገሥታት ፡ የክብርህን ፡ ጸዳል ፡ ያያሉ
አሕዛብ ፡ ለግርማህ ፡ ይሰግዳሉ
ብርሀን ፡ በርቶአልና ፡ በድቅድቁ (፫x)
ይገርማል ፡ የአንተ ፡ ጥበብ
ሰማይን ፡ ዘርግተሃል
በቃልህ ፡ ሁሉ ፡ ፀንቶአል
በቃልህ ፡ ሁሉ ፡ ፀንቶአል (፪x)
ብርቱ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ገናና ፡ ነህ ፡ ገናና (፪x)
ከፍ ፡ ያልከው ፡ ለዘላለም ፡ ገናና ፡ ነህ ፡ ገናና (፪x)
አትሻር ፡ አትለወጥ ፡ ገናና ፡ ነህ ፡ ገናና (፪x)
ከጥንትም ፡ ህያው ፡ ነበርክ ፡ ገናና ፡ ነህ ፡ ገናና (፪x)
አዝ፦ ቅጥሬ ፡ መዳን ፡ ሆኖአል ፡ ጌታ
በሬ ፡ ምስጋና
ነገሥታት ፡ የክብርህን ፡ ጸዳል ፡ ያያሉ
አሕዛብ ፡ ለግርማህ ፡ ይሰግዳሉ
ብርሀን ፡ በርቶአልና ፡ በድቅድቁ (፫x)
ከአፍህ ፡ የወጣው ፡ ቃል ፡ ገናና ፡ ነህ ፡ ገናና (፪x)
ያሻህን ፡ ይፈጽማል ፡ ገናና ፡ ነህ ፡ ገናና (፪x)
በከንቱ ፡ አይመለስ ፡ ገናና ፡ ነህ ፡ ገናና (፪x)
አይተናል ፡ ሲያረሰርስ ፡ ገናና ፡ ነህ ፡ ገናና (፪x)
አዝ፦ ቅጥሬ ፡ መዳን ፡ ሆኖአል ፡ ጌታ
በሬ ፡ ምስጋና
ነገሥታት ፡ የክብርህን ፡ ጸዳል ፡ ያያሉ
አሕዛብ ፡ ለግርማህ ፡ ይሰግዳሉ
ብርሀን ፡ በርቶአልና ፡ በድቅድቁ (፫x)
አሀዱ ፡ መጀመሪያ ፡ ገናና ፡ ነህ ፡ ገናና (፪x)
ተፈጥሮአል ፡ ባንተ ፡ ብቻ ፡ ገናና ፡ ነህ ፡ ገናና (፪x)
አይኖርም ፡ ካንተ ፡ ሌላ ፡ ገናና ፡ ነህ ፡ ገናና (፪x)
ኦሜጋ ፡ መደምደሚያ ፡ ገናና ፡ ነህ ፡ ገናና (፪x)
በኃይሉ ፡ ብርታት ፡ የገነነ
ከፍ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ያለ
ከፍ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ያለ (፬x)
|