ፍቅርህ (Feqreh) - ሳሙኤል ፡ ካሳሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሳሙኤል ፡ ካሳሁን
(Samuel Kassahun)

Samuel Kassahun 1.png


(1)

ያልተሰማ
(Yaltesema)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2013)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 6:59
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ካሳሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Kassahun)

አዝ፦ ፍቅርህ ፡ ከሞት ፡ ይልቅ ፡ ብርቱ ፡ ነው
ሕይወቴን ፡ እንደ ፡ መልሕቅ ፡ ያጸናው
መልካሙን ፡ ተስፋ ፡ ያስያዘው
በልቤ ፡ የሞላው ፡ እርሱ ፡ ነው (፪x)

ሳልወድህ ፡ ገና ፡ አንተ ፡ ወደድከኝ
የሚረባኝን ፡ አንተ ፡ አስተማርከኝ
ሳላውቅህ ፡ ገና ፡ አንተ ፡ አወቅከኝ
ከአዳኝ ፡ ወጥመድ ፡ ነጥቀህ ፡ አስጣልከኝ
እንዲህ ፡ ላረከው ፡ ምን ፡ አስቀራለሁ
በምላሽ ፡ ይኸው ፡ እዘምራለሁ (፫x)

አዝ፦ ፍቅርህ ፡ ከሞት ፡ ይልቅ ፡ ብርቱ ፡ ነው
ሕይወቴን ፡ እንደ ፡ መልሕቅ ፡ ያጸናው
መልካሙን ፡ ተስፋ ፡ ያስያዘው
በልቤ ፡ የሞላው ፡ እርሱ ፡ ነው (፪x)

በልቤ ፡ ፈሶ ፡ የአንተ ፡ ፍቅር
ጠራርጐ ፡ ያወጣል ፡ የክፋትን ፡ ዘር
ግንዱ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ መሰረት
የሕይወት ፡ ራስ ፡ የተፈጠርኩበት
ሁሉ ፡ ከርሱ ፡ ነው ፡ የሆነው ፡ ሕይወት
ትምክት ፡ የለኝም ፡ የምመካበት (፫x)

ፍቅርህ ፡ ገዢ ፡ ነው ፡ አያውቅም ፡ ክፋት
ፍጥረትን ፡ ማርኮ ፡ ያንበረከከ
ሕልውናህ ፡ ነው ፡ የአንተ ፡ ባህሪህ
ፀንቶ ፡ ሚቀጥል ፡ ከሁሉ ፡ ሚበልጥ
ሕግን ፡ ፈጽሞ ፡ የጠቀለለው
ፍቅርህ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ በደል ፡ የማይቆጥረው (፫x)