ዕልል ፡ ብዬ (Elel Beyie) - ሳሙኤል ፡ ካሳሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሳሙኤል ፡ ካሳሁን
(Samuel Kassahun)

Samuel Kassahun 1.png


(1)

ያልተሰማ
(Yaltesema)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2013)
ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 5:54
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ካሳሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Kassahun)

ዕልል ፡ እልል ፡ ብዬ (፪x)
ላከብርህ ፡ ነው ፡ ተራዬ (፪x)

ፈርዖንም ፡ ቢፎክር ፡ የመረጥከውን ፡ ሊያስገብር
ብዙ ፡ ጣረ ፡ ደከመ ፡ የአንተን ፡ ሀሳብ ፡ ሊቀይር
ትእዛዝ ፡ ወጥቶአል ፡ ከሰማይ ፡ አታቆመው ፡ በአንተ ፡ ኃይል
ላትነሳ ፡ ወድቀሃል ፡ ህዝቡን ፡ ፈቶኣል ፡ አዶናይ

የተገለጠውን ፡ ብርሃን
ሕይወት ፡ ሆኖ ፡ አየሁት ፡ በዓይኔ

መኖር ፡ መርጫለሁ ፡ ዛሬ
አቻ ፡ አልተገኘለት ፡ ክብሬ
ኦሆ ፡ ክብሬ (፪x)

አትሻር ፡ አትለወጥ ፡ የጸና ፡ ነው ፡ ዙፋንህ
አታረጅ ፡ አትደክም ፡ ትኖራለህ ፡ በክብር
ከስም ፡ በላይ ፡ ስም ፡ አለህ ፡ ከአብ ፡ ዘንድ ፡ የተሰጠህ
ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ይንበርከክ ፡ ከፍ ፡ ላለው ፡ ይስገድ

ዕልል ፡ እልል ፡ ብዬ (፪x)
ላከብርህ ፡ ነው ፡ ተራዬ (፪x)

በኃይል ፡ አይደል ፡ በብርታት
መች ፡ በራስ ፡ ነው ፡ በጥረት
በነጻ ፡ ነው ፡ ቸርነት
በእርሱ ፡ ሆነ ፡ በመንፈስ (፪x)

የተገለጠውን ፡ ብርሃን
ሕይወት ፡ ሆኖ ፡ አየሁት ፡ በዓይኔ