በእሳት ፡ የሚመልስ (Besat Yemimeles) - ሳሙኤል ፡ ካሳሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
Broom.png ይህ ፡ ጽሑፍ ፡ ገና ፡ አልተረጋገጠም ። እርማቶች ፡ ሊያስፈልጉት ፡ ይችላል ። ከቻሉ ፡ እርስዎ ፡ ያሻሽሉት
ሳሙኤል ፡ ካሳሁን
(Samuel Kassahun)

Samuel Kassahun 1.png


(1)

ያልተሰማ
(Yaltesema)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2013)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 7:28
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ካሳሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Kassahun)

ያለውን ፡ ይፈፅማል
ታማኝ ፡ ነው ፡ አይተነዋል
በእሳት ፡ የሚመልስ
እርሱ ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ ንጉሥ (፪x)

እርሱ ፡ ነው ፡ የተነሳው
እርሱ ፡ ነው ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ያለው
የኢየሱስ ፡ ነው (፪x)

ነጻ ፡ ብሎ ፡ ኢየሱስ ፡ ፈቶኛል
የከበደኝን ፡ ቀንበሬን ፡ ሰብሮአል
ሁሉ ፡ አዲስ ፡ ሆኖ ፡ ተፈጥሬአለሁ
በፀጋው ፡ ብቻ ፡ ኦሆ ፡ በእርሱ ፡ እመካለሁ

ተደርጐልኛል ፡ ኦሆሆ
መቼ ፡ በሥራ ፡ ነው ፡ ኦሆ
በፀጋው ፡ ብቻ ፡ ኦሆሆ
በእርሱ ፡ እመካለሁ (፭x)

ይጠብቁኝ ፡ ዘንድ ፡ መላእክቱን ፡ አዟል
በእሳት ፡ ቀጥሮ ፡ ያራምደኛል
ብርቱ ፡ ተዋጊ ፡ ሥሙም ፡ እግዚኣብሔር
እረኛዬ ፡ ነው ፡ ኦሆሆ ፡ መቼም ፡ አይተኛም

ብርቱ ፡ ተዋጊ ፡ ኦሆ ፡ ኦሆ
ሥሙም ፡ እግዚኣብሔር
እረኛዬ ፡ ነው ፡ ኦሆ ፡ ኦሆ
መቼም ፡ አይተኛም

ተናግሮ...

ባጠገቤ ፡ ሺህ ፡ በቀኝ ፡ አስር ፡ ሺህ
ጠላቴ ፡ ወድቆ ፡ በዓይኔ ፡ ብቻ ፡ አየሁ
ከእኔ ፡ ጋር ፡ ያለው ፡ ብርቱ ፡ ኃይል ፡ ነው
ከኃይል ፡ ወደ ፡ ኃይል ፡ ኦሆ ፡ ኦሆ ፡ እሻገራለሁ

ባጠገቤ ፡ ሺህ ፡ ኦሆ ፡ ኦሆ
በቀኝ ፡ አስር ፡ ሺህ ፡ አሄ
ከኃይል ፡ ወደ ፡ ኃይል ፡ ኦሆ
እሻገራለሁ ፡ እራመዳለሁ (፬x)

ተናግሮ...