ምን አይነት ፍቅር ነው (Min Ayenet Fikr New) (Track 8) - ሳሙኤል ቦርሳሞ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሳሙኤል ቦርሳሞ
(Samuel Borsamo)

Lyrics.jpg


(1)

እግዚአብሔር ፡ ሆይ
(Egziabher Hoy Endet Dink Ne)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፹ ፬ (1992)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 5:20
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ቦርሳሞ ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Borsamo)

ወንጀለኛ አልነበረም ነገር ግን የተጠላ
የዓለም ሃጢያት ገዶት ከክብሩ የወረደው
   አሆሆሆ አሆሆሆ
በደል የሌለው ቅጣት በርሱ ላይ ተከምሮ
እኔኑ ለማዳን ሲል በስቃይ ደቆ አሮ
   አሆሆሆ አሆሆሆ

ምን አይነት ፍቅር ነው እንደዚህ ሚያደርገው
ነፍስንስ የሚያሰጥ የትኛው ጽድቅ ነው
የእግዚአብሔር ልጅ ፍቅር ከማውቀው በላይ ነው
   አሆሆሆ አሆሆሆ

በሰው ዘንድ የተጠላ ደምግባት የሌለው ሰው
የደም ላብ እያላበው በመከራ የቆሰለው
   አሆሆሆ አሆሆሆ
ሁሉንም ማድረግ ሲችል እንደሞኝ የተናቀው
ሞቴን በሞቱ ሽሮ እኔን ሰው ያደረገው
   አሆሆሆ አሆሆሆ

ምን አይነት ፍቅር ነው እንደዚህ ሚያደርገው
ነፍስንስ የሚያሰጥ የትኛው ጽድቅ ነው
የእግዚአብሔር ልጅ ፍቅር ከማውቀው በላይ ነው
   አሆሆሆ አሆሆሆ

የጭነቀት ናዳ ዙሪያው ከጠላት ሲወርድበት
እረዳት ያጣ መስሎ ብቻውን ሆኖ ሲቃትት
   አሆሆሆ አሆሆሆ
በግፈኞቹ አመጽ ሊቆጣ የተገባው
ምንም አያውቁምና ባክህ ማራቸው ያለው
   አሆሆሆ አሆሆሆ

ምን አይነት ፍቅር ነው እንደዚህ ሚያደርገው
ነፍስንስ የሚያሰጥ የትኛው ጽድቅ ነው
የእግዚአብሔር ልጅ ፍቅር ከማውቀው በላይ ነው
  አሆሆሆ አሆሆሆ

በሰው ልጅ ችግር ፈንታ ውሎ የተቸገረው
በመከራው በሞቱ ሁሉን አንድ ያደረገው
   አሆሆሆ አሆሆሆ
የጥልን መጋረጃ ከመሃል የቀደደው
ሰው ከእግዚአብሔር ታርቆ እንዲኖር ያደረገው
   አሆሆሆ አሆሆሆ

ምን አይነት ፍቅር ነው እንደዚህ ሚያደርገው
ነፍስንስ የሚያሰጥ የትኛው ጽድቅ ነው
የእግዚአብሔር ልጅ ፍቅር ከማውቀው በላይ ነው