፬) አንድ ጊዜ አስበኝ ብዬ (And Gize Asibegn Biye) (Track 4) - ሳሙኤል ቦርሳሞ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሳሙኤል ቦርሳሞ
(Samuel Borsamo)

Lyrics.jpg


(1)

1
(1)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፹ ፬ (1992)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 7:41
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ቦርሳሞ ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Borsamo)

አንድ ጊዜ አስበኝ ብዬ
መልካሚቱ እጅህን አስተውዬ
እፎይ የምልበት ዘመን ደረሰና
እኔም በጠላቴ ራስ ላይ ቆምኩኝና
አከብርሃለሁ ዛሬም እንደገና

ብርታቱ የቱ እንደሁ ሸንግይው
በምን ይረታ ይሆን ነዝንዢው
ብሎ ለማባበል ደሊላን ላከበት
ሳምሶን መች አወቀ ጉድጓድ ሲማስበት
ሆኖም በፍጻሜው ጌታ ደረሰለት

አዝ

ብርቱ የአምላክ ጀግና ኤልያስ
የበኣልን ነቢያት ሲያተራምስ
ኤልዛቤል ገነነች ቃሏን አስረዘመች
እርሱም ዘነጋና የትናንቱን ድሎች
ጌታ አበረታው ሰጠው የእምነት ዓይኖች
አዝ

አራት መቶ ተኩል ዓመታት
ሲሰቃይ እስራኤል በባርነት
ያገለግለኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ አለው
መፈታት ታወጀ ፈርኦን ምን ይዋጠው
ትዕዛዝ ከላይ መጣ ሳይፈልግ መልቀቅ ነው
አዝ

ዮሴፍ በግዞት ውስጥ ማቀቀ
ያወቀውን አምላኩን ናፍቀ
የእንቆቅልሽ ፈቺ በጊዜው ሲያደርገው
በናቁት ሁሉ ፊት ሞገስ ሲያለብሰው
ዘመን ከመጣለት የሚቃወም ማን ነው
አዝ

መርዶኪዮስ በትዕግስት ጠበቀ
ለጊዜው የሃማም ዛቻ ጸደቀ
ያ የጥንቱ ገድል ተጽፎ ያለበት
የድል ዘመን መጣ መዝገብ ሚታይበት
የምስኪኖች አምላክ ክብር ይሁንለት

አንድ ጊዜ አስበኝ ብዬ
መልካሚቱ እጅህን አስተውዬ
እፎይ የምልበት ዘመን ደረሰና
እኔም በጠላቴ ራስ ላይ ቆምኩኝና
አከብርሃለሁ ዛሬም እንደገና