መባረክን የምታውቅ (Mebarekin Yemetawk) (Track 10) - ሳሙኤል ቦርሳሞ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሳሙኤል ቦርሳሞ
(Samuel Borsamo)

Lyrics.jpg


(1)

እግዚአብሔር ሆይ እንዴት ድንቅ ነህ
((Egziabher Hoy Endet Dinq Ne)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፹ ፬ (1992)
ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 5:57
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ቦርሳሞ ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Borsamo)

መባረክን የምታውቅ የኛ ጌታ
መዳሰስን የምታውቅ የኛ ጌታ
ዛሬም ደግመህ ጎብኘን እንደቃልህ
የኛ ስጋ ሞቶ አንተን እንድናይህ

ከጥላህ ስር ሆነን አንተን ስንጠብቅህ
የልባችንን መሻት ገልጸን ስንነግርህ
አጽናኙን ድምጽህን ህዝብህን አሰምተህ
ናና ተገናኘን ሙላን በባርኮትህ

አዝ

ጌታ አንተ ስትመጣ በልጆችህ መሃል
ያዘነ ይጽናናል ደካማ ይበረታል
በክብርህ ስትነግስ ከፍ ከፍም ስትል
የተፍገመገመ በእምነት ይሞላል

አዝ

ከሃጢያት በስተቀር በሁሉ ያለፍህ
የምስኪኖች ወዳጅ አንተ ስለሆንህ
በቀደመው ክንድህ በቀደመው ሀይልህ
ውረድ በመሃላችን ዛሬም እንደቃልህ

አዝ

የትረፈረፈ በረከት አለህና
ስብራትን ጠጋኝ ልብን የሚጽናና
የጉብኝትህን ልክ ዛሬ በዚህ አይተን
እንድትነግስልን ደግመህ ደግመህ ጎብኘን

አዝ