ይቻላል (Yechalal) - ሳሙኤል ፡ ቦርሳሞ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሳሙኤል ፡ ቦርሳሞ
(Samuel Borsamo)

Lyrics.jpg


(2)

በጌታ ፡ ሁሉ ፡ ይቻላል
(Begieta Hulu Yechalal)

ቁጥር (Track):

(7)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ቦርሳሞ ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Borsamo)

 
አዝ፦ ይቻላል ፡ አዎን ፡ ይቻላል
ይቻላል ፡ በእርግጥ ፡ ይቻላል
በእግዚአብሔር ፡ ዐይን ፡ እጅግ ፡ ቀላል ፡ ነው
እኛ ፡ ያቃተን ፡ ለእርሱ ፡ ምኑ ፡ ነው
(፪x)
ለአምላኬ ፡ ሁሉ ፡ ይቻላል
በጌታ ፡ ሁሉ ፡ ይቻላል
(፪x)

ሰላሳ ፡ ስልሳ ፡ መቶ ፡ የክፉን ፡ ሃይል ፡ አጥፍቶ
ለአምላክ ፡ ይቻላል ፡ ለአባት ፡ ይቻላል
ከልካዩን ፡ ልከለክል ፡ አዳኙን ፡ ልናድነው
ስሙ ፡ ሃያል ፡ ነው ፡ ስሙ ፡ ሃያል ፡ ነው
ችሎ ፡ የሚያስችለኝ ፡ ጌታ ፡ እያለኝ
ለምን ፡ ስንፍናን ፡ አወራለሁኝ

አዝ፦ ለአምላኬ ፡ ሁሉ ፡ ይቻላል
በጌታ ፡ ሁሉ ፡ ይቻላል (፪x)

የቀደሙት ፡ አባቶች ፡ የእምነት ፡ ምሳሌዎች
የፅድቅ ፡ አርበኞች ፡ ቆራጥ ፡ ጨካኞች
መንግሥታትን ፡ ድል ፡ ነሱ ፡ ጭፍሮችን ፡ አባረሩ
ድልን ፡ ዘመሩ ፡ በድል ፡ ዘመሩ

አዝበአምላኬ ፡ ሁሉ ፡ ይቻላል
በጌታ ፡ ሁሉ ፡ ይቻላል
(፪x)
ይቻላል ፡ አዎን ፡ ይቻላል
ይቻላል ፡ በእርግጥ ፡ ይቻላል
በእግዚአብሔር ፡ ዐይን ፡ እጅግ ፡ ቀላል ፡ ነው
እኛ ፡ ያቃተን ፡ ለእርሱ ፡ ምኑ ፡ ነው
(፪x)

የእሳትን ፡ ሃይል ፡ አለፉ ፡ ክፉውን ፡ ጥሰው ፡ አለፉ
በእምነት ፡ ድል ፡ ነሱ (፪x)
የአናብስትን ፡ አፍ ፡ ዘጉ ፡ በእምነት ፡ እያደጉ
ሄዱ ፡ ተጠጉ (፪x)

አዝ፦ ይቻላል ፡ አዎን ፡ ይቻላል
ይቻላል ፡ በእርግጥ ፡ ይቻላል
በእግዚአብሔር ፡ ዐይን ፡ እጅግ ፡ ቀላል ፡ ነው
እኛ ፡ ያቃተን ፡ ለእርሱ ፡ ምኑ ፡ ነው
(፪x)
ለአምላኬ ፡ ሁሉ ፡ ይቻላል
በጌታ ፡ ሁሉ ፡ ይቻላል
(፪x)

ሃይልን ፡ በሚያስታጥቀን ፡ በአምላካችን ፡ ታምነን
እንገባለን ፡ እንወጣለን
ቃሉም ፡ እንደሚነግረን ፡ በእርሱ ፡ ከአሸናፊዎች
እንበልጣለን ፡ እንበልጣለን
ችሎ ፡ የሚያስችለኝ ፡ ጌታ ፡ እያለኝ
ለምን ፡ ስንፍናን ፡ አወራለሁኝ

አዝ፦ ለአምላኬ ፡ ሁሉ ፡ ይቻላል
በጌታ ፡ ሁሉ ፡ ይቻላል (፪x)

እንወራረዳለን ፡ ለምስሉ ፡ አንሰግድም
ጌታ ፡ ይረዳናል (፪x)
እውነትን ፡ እንሸሽግም ፡ በወንጌል ፡ ደግሞ ፡ አናፍርም
ኢየሱስ ፡ ያድናል (፪x)

አዝ፦ ይቻላል ፡ አዎን ፡ ይቻላል
ይቻላል ፡ በእርግጥ ፡ ይቻላል
በእግዚአብሔር ፡ ዐይን ፡ እጅግ ፡ ቀላል ፡ ነው
እኛ ፡ ያቃተን ፡ ለእርሱ ፡ ምኑ ፡ ነው
(፪x)
ለአምላኬ ፡ ሁሉ ፡ ይቻላል
በጌታ ፡ ሁሉ ፡ ይቻላል
(፬x)