From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ደስታችን ፡ በምድር ፡ ፍፁም ፡ ባይሆን ፡ እንኳን
ልባችን ፡ ሲመታ ፡ በመከራ ፡ ሃዘን
የጌታን ፡ መገለጥ ፡ በመጠበቃችን
የምንጽናናበት ፡ አዲስ ፡ አገር ፡ አለን
አዝ፦ ተንቀን ፡ አንቀርም ፡ ተጥለን ፡ በምድር
አዲስ ፡ አገር ፡ አለን ፡ ከአድማስ ፡ ባሻገር
ጌታም ፡ ይመለሳል ፡ ዳግም ፡ ሊያሳርፈን
በገዛ ፡ ዙፋኑ ፡ በቀኝ ፡ ሊያስቀምጠን
የምድር ፡ መጽዐተኛ ፡ ባለ ፡ ፅኑ ፡ ተስፋ
በላይ ፡ ያለው ፡ ሽቶ ፡ በምድር ፡ የተገፋ
ባይደላውም ፡ እንኳን ፡ ፀንቶ ፡ በመታገስ
በክብር ፡ ያየዋል ፡ የናፈቀውን ፡ ንጉሥ
አዝ፦ ተንቀን ፡ አንቀርም ፡ ተጥለን ፡ በምድር
አዲስ ፡ አገር ፡ አለን ፡ ከአድማስ ፡ ባሻገር
ጌታም ፡ ይመለሳል ፡ ዳግም ፡ ሊያሳርፈን
በማያልፈው ፡ መንግሥት ፡ ዘለዓለም ፡ ሊያነግሰን
የዚህን ፡ ዓለም ፡ ሃሳብ ፡ ታግሎ ፡ ያሸነፈ
በመከራ ፡ ፀንቶ ፡ በትዕግሥት ፡ ያለፈ
አምላኩ ፡ ሲገለጥ ፡ እጅጉን ፡ ይፅናናል
ያልተሰማ ፡ ዜማን ፡ ውዳሴን ፡ ያፈልቃል
አዝ፦ ተንቀን ፡ አንቀርም ፡ ተጥለን ፡ በምድር
አዲስ ፡ አገር ፡ አለን ፡ ከአድማስ ፡ ባሻገር
ጌታም ፡ ይመለሳል ፡ ዳግም ፡ ሊያሳርፈን
በማያልፈው ፡ መንግሥት ፡ ዘለዓለም ፡ ሊያነግሰን
መከራም ፡ ይረሳል ፡ ሃዘንም ፡ ይቀራል
ያናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ ፡ እምባችንን ፡ ያብሳል
ጻድቅ ፡ ፈራጃችን ፡ በቅርብ ፡ ይገለጣል
የወጉትም ፡ ዐይኖች ፡ ፊት ፡ ለፊት ፡ ያዩታል
አዝ፦ ተንቀን ፡ አንቀርም ፡ ተጥለን ፡ በምድር
አዲስ ፡ አገር ፡ አለን ፡ ከአድማስ ፡ ባሻገር
ጌታም ፡ ይመለሳል ፡ ዳግም ፡ ሊያሳርፈን
በገዛ ፡ ዙፋኑ ፡ በቀኝ ፡ ሊያስቀምጠን (፪x)
|