ሲንከባለል (Sinkebalel) - ሳሙኤል ፡ ቦርሳሞ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሳሙኤል ፡ ቦርሳሞ
(Samuel Borsamo)

Lyrics.jpg


(2)

በጌታ ፡ ሁሉ ፡ ይቻላል
(Begieta Hulu Yechalal)

ቁጥር (Track):

(4)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ቦርሳሞ ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Borsamo)

 
አዝ፦ በረጅም ፡ ዘመን ፡ የፈሰሰ ፡ እምባ
ወደ ፡ ላይ ፡ ሰንጥቆ ፡ አርያም ፡ ሲገባ
ጌታም ፡ ዘንበል ፡ ሲል ፡ ይታየኛል ፡ እኔ
የተናገረውን ፡ ሲፈፅም ፡ በዐይኔ

ሲንከባለል ፡ ድንጋዩ
ጠልን ፡ ሲሰጥ ፡ ሰማዩ
የምድር ፡ ፍሬ ፡ ሲለምልም
ጻድቅ ፡ በምሥጋና ፡ ይግነን (፪x)

አዝ፦ በረጅም ፡ ዘመን ፡ የፈሰሰ ፡ እምባ
ወደ ፡ ላይ ፡ ሰንጥቆ ፡ አርያም ፡ ሲገባ
ጌታም ፡ ዘንበል ፡ ሲል ፡ ይታየኛል ፡ እኔ
የተናገረውን ፡ ሲፈፅም ፡ በዐይኔ

ምናምንቴው ፡ ተራግፎ
የከበረው ፡ ተሰልፎ
ጌታን ፡ ያየ ፡ በክብር
እንዲህ ፡ ይበል ፡ ከእኔ ፡ ጋር (፪x)

አዝ፦ በረጅም ፡ ዘመን ፡ የፈሰሰ ፡ እምባ
ወደ ፡ ላይ ፡ ሰንጥቆ ፡ አርያም ፡ ሲገባ
ጌታም ፡ ዘንበል ፡ ሲል ፡ ይታየኛል ፡ እኔ
የተናገረውን ፡ ሲፈፅም ፡ በዐይኔ

ይሽሩን ፡ ሆይ ፡ ብሎታል
በቁልምጫ ፡ ጠርቶታል
በደመናት ፡ እንደሚሄድ
እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ የለም (፪x)

አዝ፦ በረጅም ፡ ዘመን ፡ የፈሰሰ ፡ እምባ
ወደ ፡ ላይ ፡ ሰንጥቆ ፡ አርያም ፡ ሲገባ
ጌታም ፡ ዘንበል ፡ ሲል ፡ ይታየኛል ፡ እኔ
የተናገረውን ፡ ሲፈፅም ፡ በዐይኔ

ሲቆረቆር ፡ ምሥጋና
ተኖ ፡ ሲሄድ ፡ በደመና
ያሸተዋል ፡ መስዋዕቴን
እኔም ፡ ላብዛ ፡ ምሥጋናዬን (፪x)

አዝ፦ በረጅም ፡ ዘመን ፡ የፈሰሰ ፡ እምባ
ወደ ፡ ላይ ፡ ሰንጥቆ ፡ አርያም ፡ ሲገባ
ጌታም ፡ ዘንበል ፡ ሲል ፡ ይታየኛል ፡ እኔ
የተናገረውን ፡ ሲፈፅም ፡ በዐይኔ